top of page

(ኢትዮ 360-ግንቦት 24/2015) በደብረማርቆስና በደምበጫ ህዝባዊ እምቢተኝነቱ እንደቀጠለ ነው።



የደብረማርቆስ ከተማ ነዋሪ ለሁለተኛ ቀን እምቢተኝነቱን ሲቀጥል የደምበጫ ነዋሪም ይሄንን ትግል መቀላቀሉን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።



ደብረማርቆስ ላይ የንግድ ሱቆችን በግዴታ ለማስከፈት ነዋሪውን የሚያዋክበው የብአዴኑ ካድሬ ደምበጫ ላይም ወጣቶችን በማስደብደብና በማሳሰር ላይ መሆኑን ይናገራሉ።



ይሄን ድብደባ እየፈጸመ ያለው ደግሞ በአካባቢው የተሰማራውና የፖሊስን፣ የሚሊሻንና የአድማ ብተናን ስም የያዘው ስብስብ ነው ይላሉ።



ደንበጫ ላይ ወጣቶችን እየደበደበ እያሰረ ያለው ይሄው የህገወጡ ቡድን ስብስብ ከማህበረሰቡ ከባድ ተቃውሞ እንደገጠመውም ሳይጠቁሙ አላለፉም።



በዚህ ሁሉ ትግል ውስጥ ደግሞ ሆቴሎቻቸውን ባለመዝጋት የዚህ ቡድን መሰባሰቢያ በማድረግና ሌሎችንም በማሳመጽ የሚንቀሳቀሱ ሆድ አደር ባለሃብቶችና ካድሬዎች የአማራ ህዝብ ለእርድ እያቀረቡት ነው ሲሉም ያለውን ሁኔታ ገልጸውታል።



ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ የኦህዴዱ መከላከያ ሃይል በሚዳ ወረዳ በንጹሃን ዜጎች ላይ ተኩስ መክፈቱን ተናግረዋል።



ሰሞኑን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሃይሉን ወደ አካባቢው ሲያግዝ የከረመው ይሄው አካል ዛሬ በግልጽ ጦርነት መክፈቱን ይናገራሉ።


ይሄ ቡድን እየፈጸመ ያለው ወንጀል ያስቆጣው የአካባቢው ማህበረሰብ ፊት ለፊት ከዚህ ሃይል ጋር መፋጠጡን አመልክተዋል።



በአካባቢው ያለው የፋኖ ህዝባዊ ሃይልም ወገኖቹን ላለማስነካት ከዚሁ ቡድን ጋር ፊት ለፊት መጋጠሙንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።



ህብረተሰቡ ከዚህም አልፎ ይሄ ቡድን አልፎ ወደ ሌላ አካባቢው እንዳይሄድ መንገድ በመዝጋት ጭምር እየተከላከለ መሆኑንም አመልክተዋል።



በተያያዘ ዜና ለሊቱን ሲጓዝ ያደረው የኦህዴዱ የመከላከያ ሃይል ወደ ሞረትና ጅሩ በማምራት ጅሁር ቀበሌን መውረሩንም ምንጮቹ አመልክተዋል።



ህብረተሰቡም በድንገት መቶ አካባቢውን የወርረውን ሃይል እየተከታተለው መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

Comments


bottom of page