በደብረ ኤልያስ የኦህዴዱ መከላከያ ስብስብ ጉዳት ያደረሰባቸውን መነኮሳትንና ምእመናንን ለመታደግ አሁንም ከባድ ችግር እንደገጠማቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢትዮ 360 ገለጹ።
እስካሁን ከአንዱ መግቢያ ወደ አንዱ መግቢያ በመሄድ ከባድ ጥረት ተደርጎ እስካሁን መርዳት የቻሉት ወደ 150 ምእመናንን ብቻ መሆኑን ይናገራሉ።
በከባድ ፈተና ከቦታው የወጡትን ምእመናንም ለሊትቱን ላይ አንድ ቦታ እንዲጠለሉ ካደረጉ በኋላ አሁን ወደ ሌላ አካባቢ እንዲሄዱ መደረጋቸውንና ለሌቹን ደግሞ ህብረተሰቡ በተቻለው አቅም ለመርዳት እየሞከረ መሆኑን ገልጸዋል።
በገዳሙ በሌላኛው አቅጣጫ ደግሞ ከገዳሙ የተረፉ ምእመናን ምንም አይነት ድጋፍ እንዳያገኙ ተደርገው መታገታቸውን አመልክተዋል።
ገዳሙን ሙሉ በሙሉ ያወደመው ይሄው ቡድን አሁንም የገዳሙን እህልና ንብረት ማጋዙን ቀጥሏል ብለዋል።
ያለው ሁኔታ ከባድ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ምን ያህል ሰው እንኳን እንደተጎዳ ማወቅ አልተቻለም ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።
ከባድ ጫና እየተደረገበት ያለው ማህበረሰብ በተለይ በገዳሙ ምዕራብ በኩል የተጎዱትን ለመታደግ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑንም ይናገራሉ።
የተጎዱ ወገኖቻቸውን ለመታደግ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ያለው ማህበረሰብ በሸክም የሚሄዱ ወገኖቹን ሁሉ ከአካባቢው ለማውጣት መሞከሩን ገልጸዋል።
እስካሁን ባደረጉት ጥረትም ወደ 150 የሚሆኑ ምእመናንን ከአካባቢው እንዲወጡ ማድረጋቸውን ይናገራሉ።
በገዳሙ የአብነት ተማሪ ከነበሩት 40 ከሚሆኑ ህጻናት በህይወት የተረፉት 8 ያህሉ ናቸው ሲሉም ይናገራሉ።ከነዚህ መሃል ጉዳት የደረሰባቸውን አግኝተው ድጋፍ እያደረጉላቸው መሆኑንም ገልጸዋል።