የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ነገ በድጋሚ ተቃውሞ ሊያስነሳ ይችላል በሚል በርካታ የእምነቱ ተከታዮች እየታሰሩ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።
ከኦህዴዱ ስርአት ህገወጥ የቤትና መስጂድ ፈረሳ ጋር በተያያዘ ነገ ከጁምአ ስግደት በኋላ ተቃዉሞ ይኖራል በሚል በፍርሃት እየራደ ያለው አካል ምናልባትም ነገ የጁምአ ጸሎት እንዳይኖር ሊከለክል ይችላል ሲሉም ዛሬ ላይ እየታየ ያለውን አዝማሚያ አመልክተዋል።
ሌላዉ ይላሉ ምንጮቹ በነገዉ ዕለት መርካቶ ሙሉ ህንፃዎች ላይ ስራ የለም በሚል መደብራቸውን እንዲዘጉ አስገዳጅ ትዕዛዝ መሰጠቱንም ተናግረዋል፡፡
ከዛም አልፎ ስራ የለም የሚል የማስጠንቀቂያ ወረቀቶች በየህንፃዎቹ እየለጠፈ ያለው አካል በየቦታው ካሜራዎችን ገጥመናል የሚሉ መልዕክቶችን በመለጠፍ ላይ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ይሄንን ሁሉ ማስፈራሪያ እየሰጠ ያለውና በፍርሃት ሊፈርስ የደረሰው የኦህዴዱ አገዛዝ ያሰማራው ቡድን ቤት ለቤት ሳይቀር ዋና ናቸው የሚባሉ የእምነቱ ተከታዮችን እያሳደደ መሆኑን ነው የኢትዮ 360 ምንጮች የተናገሩት።