top of page

(ኢትዮ 360-ግንቦት 3/2015) በሰሜኑ ጦርነት ወደ አካባቢው ተልከው የነበሩ የመከላከያ አባላት ወደቤተሰባቸው አልተመለሱም።



በሰሜኑ ጦርነት ወደ አካባቢው ተልከው የነበሩ የመከላከያ አባላት ቤተሰቦች እስካሁን ልጆቻቸው ያሉበት ሁኔታ መወቅ እንዳልቻሉ ለኢትዮ 360 ገለጹ።


በተደጋጋሚ ስለልጆቻቸው እንዲነግሯቸው የሚመለከታቸውን አካላት ለማነጋገር ቢሞክሩም ሰሚ ማግኘት እንዳልቻሉ ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አስፍረዋል።


የአንዳንዶቹ ልጆቻቸው በጦርነቱ ወቅት መማረካቸውን ቢሰሙም እስካሁን ግን ልጆቻቸውን ለማስመለስ የሞከረ አካል እንደሌለም ይናገራሉ።


ሌሎቹ ወላጆች ደግሞ እስካሁን የልጆቻቸው ደብዛ እንደጠፋ መሆኑን በመረጃቸው ላይ አመልክተዋል።


ቤተሰቦቻቸው እንደሚሉት በጦርነቱ ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ሃይል መማረኩን እንዲሁም መገደሉን ሰምተዋል።


ነገር ግን ከሁለት አመት በላይ ልጆቻቸው ስላሉበት ሁኔታ የሚነግራቸው አካል ማግኘት እንዳልቻሉ አስታውቀዋል።


ልጆቻቸው በጦርነቱ ወቅት ተሰውተውም ከሆነ እንደወጉ የልጆቻቸውን መርዶ መስማት እንዳይችሉ መደረጋቸውን ነው የሚያነሱት።


በተለይ ደግሞ በምርኮኛ ስም እስካሁን እየተሰቃዩ ያሉ ልጆቻቸውን ተስማማን ያሉት አካላት ሊለቁላቸው እንደሚገባም ነው በመረጃቸው ላይ ጥሪያቸውን ያቀረቡት።


ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ንጹሃን ዜጎች ባለቁበት በሰሜኑ ጦርነት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ሃይልም መገደሉንና ለከፋ የአካል ጉዳት መዳረጉን ከዛም አልፎ በሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ በምርኮኛ ስም ታግተው እንደሚገኙም በተደጋጋሚ ሲገለጽ መቆየቱንም ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አስፍረዋል።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

bottom of page