በአማራ ክልል የተጀመረውንና አልሳካ ያለውን ዘመቻ በድጋሚ በምስራቅ አማራ ፋኖና በጎጃም የፋኖ ህዝባዊ ሃይል ላይ ዳግም ለመጀመር እንቅስቃሴ መጀመሩን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
በተደጋጋሚ የምስራቅ አማራ ፋኖ አመራሮችን ለማፈንና ሰራዊቱንም ለመምታት እየለፋ ያለው የኦህዴዱ ኦነግ መሪ ለምን ተሸነፍን በሚል ተደጋጋሚ ስብሰባ እያደረገ መሆኑን ያነሳሉ።
እነ አርበኛ መሳፍንትንም በሽምግልና ማሸነፍ ያልቻለው አብይ አህመድ አሁን በአዲስ መልክ ሊጀምረው ያሰበውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በጎጃምና በምስራቅ አማራ ፋኖ ላይ ለማድረግ ተንቀሳቅሷል ብለዋል።
በተለይ በመካነሰላም፣በደብረወርቅና በሞጣ በኩል ሃይሉን እያጋዘ ያለው የኦህዴዱ ኦነግ አገዛዝ በሸዋ በኩልም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ገዳይ ቡድኑን ማሰማራቱንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ዛሬ ወሪያ በረሃ ላይ የፋኖ ህዝባዊ ሃይል አባላትን በአካባቢው አድማ ብተናና ሚሊሻ ማስከበቡንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
የአባይ በረሃን ጨምሮ መርጦ ለማርያምንና ግንደ ወይን አካባቢውን አናስነካም ያለው ማህበርሰብ መንገድ መዝጋት መጀመሩን ነውም ምንጮቹ የሚናገሩት።
የአማራ ክልልን ሙሉ በሙሉ አስከብቤያለው ብሎ የሚያብሰው አብይ አህመድ በአዲስ መልክ ሊጀምረው ያሰበውን ጥቃት ዛሬ ዳር ዳር ማለት መጀመሩንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
Comments