top of page

(ኢትዮ 360-ግንቦት 3/2015) በአማሮ ልዩ ወረዳ የኮሌራ ወረርሽኝ የአምስት ንጹሃንን ህይወት ቀጠፈ።



በአማሮ ልዩ ወረዳ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ ባለፉት 48 ሰአታት ብቻ የአምስት ንጹሃንን ህይወት መቅጠፉ ተሰማ።


በተደጋጋሚ በአካባቢው በየጊዜው የኦነግ ታጣቂ ቡድን ከሚፈጸመው የንጹህን ግድያና ማሳደድ ጋር ተያይዞ ህብረተሰቡ ለከፋ ችግር ተጋልጦ መቆየቱን ኢትዮ 360 በተደጋጋሚ በመረጃው ማውጣቱ ይታወሳል።


በህብተሰቡ ላይ የሚደርሰው ችግር ተባብሶም መሬታቸውን ማረስና ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ወደማይችሉበት ደረጃ መሸጋገራቸውንም አስታውቆ ነበር።


ምናልባትም ይሄ ችግር ከአማሮ አልፎ በጉጄና በሌሎች አካባቢዎች ከመስፋፋቱ ጋር ተያይዞ ረሃብ ሊከሰትና የተለያዩ ወረርሽኞችንም ሊያስከትል እንደሚል በተደጋጋሚ ኢትዮ 360 ሲያነሳው መቆየቱንም ያስታውሳሉ።



ከዚሁ ጋር ተያይዞም የኮሌራ ወረርሽኝ በአማሮ ልዩ ወረዳ ከባለፈው ሚያዚያ ጀምሮ መከሰቱንና በርካታ ንጹሃን ዜጎችን ለጉዳት መዳረጉን የኢትዮ 360 ምንጮች ይናገራሉ።


የልዩ ወረዳው ጤና ጽህፈት ቤት ችግሩ ከሚያዚያ ጀምሮ መከሰቱን አምኖ በዚህም በ48 ሰአታት ውስጥ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉን ማመኑን ያነሳሉ።


ነገር ግን ጽህፈት ቤቱ ይሄን ይመን እንጂ ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ ህይወታቸው ያለፈውም ሆነ ለከፋ ህመም የተዳረጉት ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ያነሳሉ።


ጽህፈት ቤቱ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ቢገልጽም ሃገሪቱ ከገጠማት የውጭ ምንዛሪ እጥረት ጋር ተያይዞ የህክምና መገልገያ መሳሪያም ሆነ የመድሃኒት አቅርቦት በበቂ ሁኔታ ማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል ሲሉ እውነቱን ይናገራሉ።



ምናልባትም ይላሉ ምንጮቹ አማሮ ላይ የተከሰተው ወረርሽኝ ወደሌሎቹ አካባቢዎች መዛመቱን የሚያሳዩ ምልክቶች መታየታቸውንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


በአካባቢው ነዋሪው መሬቱን እንዳያርስ፣የሚመገበውንም ሆነ ህክምና እንዳያገኝ ተከልክሎና በሺዎች የሚቆጠረው ከቤቱ ከተፈናቀረ ድፍን አራት አመታት ያህል ማስቆጠሩንም የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።



Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

bottom of page