top of page

ኢትዮ 360-ግንቦት 3/2015) በደብረብርሃን የአካባቢው ሚሊሻ በአካባቢው ማህበረሰብና በፋኖ ህዝባዊ ሃይል ላይ ጥቃት ሊፈጽም ነው።


በደብረብርሃን አዳዲስ የአማራ ልዩ ሃይልን ልብስ እንዲለብስ የተደረገው የአካባቢው ሚሊሻ በአካባቢው ማህበረሰብና በፋኖ ህዝባዊ ሃይል ላይ ጥቃት እንዲፈጽም እየተዘጋጀ ነው ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።


ከዛም አልፎ ይላሉ ምንጮቹ ከየወረዳው በሚሊሻ ስም ያሰባሰባቸውን ቡድኖች ወደ ሸዋ ሮቢት ሔደው የፋኖ ህዝባዊ ሃይልንም ሆነ ከእሱ ጋር አብረው በሚቆሙት ላይ ጦርነት እንዲከፍቱ እያዘጋጀ ነው ሲሉም አጋልጠዋል።


በሁሉም በኩል እቅዱ ያልተሳካለት የኦህዴዱ አገዛዝና ሆድ አደሩ የብአዴን ካድሬ የሸዋ ህዝብን እርስ በርሱ ለማፋጀት ተዘጋጅቷል ብለዋል።


የአማራ ልዩ ሃይልን ልብስ ኣንዲለብ እየተደረገ ያለው ይሄ ስብስብ አስቀድሞ ከየቦታው እንዲሰባሰብና በተለያዩ ጥቅሞች እንዲደለል የተደረገ መሆኑንም ያነሳሉ።


ከዚህ ሁሉ ድለላ በኋላ ወገኖችን ውጋ ሲባል ይወጋል ወይንስ ከነሙሉ መስሳሪያው ድለላው ሳያታልለው ወገኔን አልወጋም ብሎ እንደተበተነው እውነተኛው ልዩ ሃይል ይሆናል የሚለው ሌላው አነጋጋሪ ጉዳይ ነው ብለዋል።


ደብረብርሃን እየሆነና እየተፈጸመ ያለው አማራውን አርስ በርስ ያማስጨረሱ ዘመቻ የሚመራው በከተማዋ አስተዳዳሪና በአጠገቡ ባለ የካድሬዎች ስብስብ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ በመሀል ሜዳ ከተማ ከትላንት ጀምሮ በከተማ ውስጥ ያሉ ሆቴሎችና ፔኒሲዎኖች በመበርበር ላይ ናቸው ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች አመልክተዋል።


ለዚህ ሁሉ ትርምስ ምክንያቱ ደግሞ በርካታ ወታደሮች የያዘ መቶ አለቃ ከነመሳሪያው ተሰውሯል በሚል መሆኑን ያነሳሉ።


መቶ አለቃው ከፍተኛ ቁጥር ካለው ሰራዊት ጋር የት እንደገባ ባይታወቅም አሳሹ ብ ቡድን ግን ከሆቴሎች አልፎ ወደ አውቶብስ መናሃሪ ድረስ በመሄድ ህዝቡን እያሰቃየ ነው ይላሉ።


በአውቶቡስ መናሃሪያ ውስጥ ፍተሻ ማካሄድ ብቻ ሳይሆን የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶቹ ለግዳጅ ይፈለጋሉ በሚል እየተወሰዱ መሆኑንም አመልክተዋል።


ከጥቂቱ ውጪ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከመነሳሪያው የተበተነው የአማራ ልዩ ሃይል ጉዳይ እንቅልፍ የነሳው አብይ አህመድ የኔ ሰራዊት ናቸው ብሎ ወደ አካባቢው የላካቸው በሺዎች የሚቆጠሩ የመከላከያ አባላት ከነበመሳሪያቸው የመክዳታቸው ጉዳይ ቤተመንግስቱን ንጦታል ብለዋል።


እናም በክልሉ በተለያዩ አካባቢው ተበትኖ እነዚህን ሃይሎች ሲፈልግ የሚውለው ሆድ አደር ካድሬና የኦህዴዱ የደህንነት ቡድን ከማህበረሰቡ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው መሆኑንም ምንጮቹ ሳይጠቁሙ አላለፉም።


Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አስፍረዋል። ከዚህ በፊት ይሄው ተመሳሳይ ድርጊት የትግራይ ተወላጅ በሆኑ የአየር

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ ቡድን አሁን አንድ ቦታ በከተማው ፒያሳ ተብሎ በሚጠራውና ደሴ መውጫ ላይ ብቻ መሆኑን ነው የተናገሩት

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰ

Comments


bottom of page