የፌደራሉ ፖሊስ መስሪያ ቤት በከባድ ውጥረት ውስጥ መግባቱን የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች ገለጹ።
የውስጥ ምንጮቹ የፌደራል መስሪያ ቤቱ በቀን ሶስት ጊዜ ስብሰባ እየተካሄደ መሆኑን ያነሳሉ።
ስብሰባው በቀን ሶስት ጊዜ ይጠራ እንጂ ዋናው አጀንዳ ግን ጽንፈኛው ፋኖ ሃገር እያሰበረ ነው፣ከመሃከላችሁ የጽንፈኛው ፋኖ ደጋፊ የሆነውን አውጡ የሚል መሆኑን አመልክተዋል።
በዚህ ስብሰባ ላይ ታላቁ መሪ ለሀገር ጠቃሚዉ በሚል በተደጋጋሚ ስሙ የሚነሳው ግርማ የሺጥላ የተገደለው በዚሁ ቡድን ነው፣ስለዚህ ይሄን ቡድን የሚደግፈውን አጋልጡ በሚል የሰራተኛውን መከራ አብዝተውታል ይላሉ የውስጥ ምንጮቹ።
ይሄ ሁሉ ማስፈራሪያና ዛቻ ሲሰነዘር በስብሰባው ላይ ከነበረው የአማራ ተወላጅ አንድም ሰው ምላሽ ሳይሰጣቸው ቀጥሏል ብለዋል።
የሌላው ብሔር ተወላጆች ነን የሚሉ አመራሮች ስራ ተረጋግቶ መስራት አልተቻለም፣ አንድ ሀገር አንድ ባንድራ ነዉ ያለን፣ ስለክልል ስለማይማኖት አይመለከተንም በሚል ለማሞኘት ቢሞክሩም ምላሱ ግን ያው ዝምታ ነው ሲሉ የውስጥ ምንጮቹ ገልጸዋል።
ነገር ግን እነሱ ይሄን ይበሉ እንጂ ውሎና አዳራቸው የት እንደሆነ የሚያውቀው ተራው ሰራተኛ ግን ስብሰባውን በዝምታ ከመታዘብ ውጪ አንድም ያለው ነገር የለም ሲሉ አስቀምጠዋል።
በቀን ሶስት ጊዜ ሰራተኛውን በስብሰባ እየምሰ ያለው ይሄው የኦነጉ ኦህዴድ ስብስብ በጎን በኩል የአማራ ተወላጅ የሆኑ መኮንኖችን ምክንያት እየፈለገ ወደ እስር በማጋዝ ላይ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ሰራዊቱን ማታለያ ተደርጎ እየተወራ ያለው ሌላ ነገር ደግሞ የአባይ ግድብ እያለቀ ነው፣ሽያጭም ጀምረናል ስለዚህ ሃገርን ማረጋጋት ስላለብን ጽንፈኛው ፋኖ ላይ በጋራ እንነሳ የሚል መሆኑን ያነሳሉ።
በሁሉም ስብሰባ ላይ የማይዘለለው ሌላ ጉዳይ ቢኖር ኢትዮ 360ን ታያላችሁ፣እሱን አቁሙ ምክንያቱም እነሱ ሃገርን ለማፍረስ የሚሰሩ አሸባሪዎች ናቸው የሚል መሆኑን የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች ተናግረዋል።
Comments