top of page

ኢትዮ 360-ግንቦት 30/2015) በሰሜን ሸዋ የተለያዩ አካባቢዎች አዲስ ጥቃት ሊከፈት ነው።


በሰሜን ሸዋ የተለያዩ አካባቢዎችን ወሮ የሚገኘው የኦህዴዱ ሃይል አሁንም አዲስ ጥቃት ለመክፈት በዝግጅት ላይ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።


በሸዋ ሮቢት ራሳ፣በሚዳ ወረዳ፣በማጀቴና አካባቢው ተደጋጋሚ ጥቃት ያደረገው ይሄው ቡድን አሁንም አዲስ ጦርነት ለመክፈት በዝግጅት ላይ መሆኑን ይናገራሉ።


የእንሳሮና አካባቢውን በዚሁ ሃይል እንዲወረር ያደረገው አካል ወደ ሞረትና ጅሩ ወረዳ ማምራቱንም ጠቁመዋል።


በሁሉም አካባቢዎች ሃይሉን እያሰማራ ያለው ይሄው ገዳይ ቡድን ለዚህ የሚሰጠው ምክንያት ደግሞ የፋኖ ህዝባዊ ሃይል በብዛት በአካባቢዎቹ አለ የሚል መሆኑንም ያስቀምጣሉ።


የፋኖ ህዝባዊ ሃይልን በገዛ መሬቱና ቤቱ ሊወጋው የመጣው ሃይል ጦርነት ለመክፈት ከሚያደርገው ዝግጅት ጎን ለጎን አፈናውንም አጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።


በተለይ በብአዴኑ አመራርና ለሆዱ ያደረ ሚሊሻና አድማ ብተና የሚባለው ቡድን ደግሞ መንገድ ከመምራት ጀምሮ የራሱን ወገኖች በጥቆማ እስከማስያዝና እስከማስገደል ያለውን የክህደት ተግባር መፈጸሙን ቀጥሏል ብለዋል።


በተለያዩ አቅጣጫዎች የአማራውን ህዝብ ለመጨረስ ጦርነት የከፈተውና መንግስት ነኝ ብሎ ራሱን የሚጠራው አካል እስካሁን የከፈተው ዘመቻ አልሳካ ሲለው አሁን ደግሞ በአዲስ መልኩ ጥቃት ለመክፈት እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።


አሁን ደግሞ አይኑና ትኩረቱን በወልቃይትና ራያ ያደረገው አካል በዛ አቅጣጫ ሃይሉን አስጠግቶ ከሚጠብቀው የህወሃት ቡድን ጋር በጋራ በመሆን አማራው ላይ ጦርነት ለመክፈት ሙከራ እያደረጉ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

Comments


bottom of page