ፌደራል ላይ የተቀመጠው አካል በድጋሚ አርበኛ ዘመነ ካሴን ለማሰር እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።
የብአዴኑ ብልጽግና አርበኛ ዘመነ ካሴ ላይ እስከአሁን የፈጠራቸው የሀሰት ክሶች በሕግ ፊት ከሽፈውና ሀሰትነታቸውም ተረጋግጦ፤ ከዘጠኝ ወራት የፖለቲካ እስራት በኋላ አርበኛ ዘመነ ካሴ ከባሕር ዳር ማረሚያ ቤት የወጣው ከሁለት ቀን በፊት ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓ.ም እንደነበርም ምንጮቹ ያስታውሳሉ።
የዘመነ ካሴን የሃሰት ክስ ሲመለከቱ የቆዩት የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችም በዚህ ጉዳይ ላይ አርበኛ ዘመነ ካሴን መክሰስ አንችልም፤ ተገቢም አይደለም፤ ይሄን ጉዳይ በተደጋጋሚ ስለተመለከትነው ፍርድ ለመስጠት አንቀመጥም የሚል ቁርጥ ያለ ውሳኔ ማሳለፋቸውም የተሰማሁ በነዚሁ ቀናቶች እንደነበር ያነሳሉ።
የክልሉ ከፍተኛ ዳኞች አቋም ያናደደው የኦህዴዱ ስብስብም ፌደራል ላይ እንደ አዲስ ክሱን በማቅረብ ለአርበኛ ዘመነ ካሴ መጥሪያ ለመስጠት እየተረባረቡ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ለአርበኛው የመጥሪያ ወረቀት መስጠት ብቻ ሳይሆን አፍኖ ለመውሰድም እቅድ መያዙን ጠቁሙዋል።
አርበኛ ዘመነ ካሴ ከእስር መውጣትን ተከትሎ ከህዝቡ የተሰጠውን ምላሽ ያየውና በፍርሃት እየራደ ያለው አብይ አህመድ በተቻለ አቅም ሁሉ እስክንድር ነጋንና አርበኛ ዘመነ ካሴን ለማጥፋት እንቅልፉን ማጣቱን ምንጮቹ ይናገራሉ።
ከዚህ ፍርሃቱ ለመውጣቱም ሰሞኑን እስክንድር ነጋ እንዲገደል ትእዛዝ ሲያሳልፍ አሁን ደግሞ አብረኛ ዘመነን አፍኖ ወደ ፌደራል ለመውሰድ ካልሆነም ለመግደል መመሪያ አውርዷል ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ተናግረዋል።