top of page

ኢትዮ 360-ግንቦት 8/2015) በአዲስ አበባ ከተማ በጉልት የችርቻሮ ንግድ የተሰማሩ ነዋሪዎች የንግድ ቦታ እየፈረሰ ነው።


በአዲስ አበባ ከተማ በጉልት የችርቻሮ ንግድ የተሰማሩ ነዋሪዎች የንግድ ቦታ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ሲፈርስ መዋሉን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።


በተለይ በቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኘውና ለረጅም አመታት እነዚህን ነጋዴዎች ይዞ የቆየው የየረር ጉሊት የንግድ ቦታ ዛሬ ሲፈርስ መዋሉንም ምንጮቹ ያነሳሉ።


ይሄንን አካባቢው የማፍረሱ ትእዛዝ በዋናነት የወረደው ከከተማዋ ከንቲባ ቢሮ ሲሆን ዋና አለማውም በአረንጓዴ ልማት ስም ለባለጊዜ ባለሃብቶች ለማደል ነው ይላሉ።


የነባሯንና የጥንቷን አዲስ አበባ ከለር ለመቀየር እየተሯሯጠ ያለው የኦህዴድ መራሹ ስርአት የንግድ ቦታዎችንና መኖሪያ ቤቶችን በማፍረስ ብቻ ሳይሆን አይን ባወጣ ሌብነት ላይም የተሰማራ ስርአት ነው ሲሉም እየተሰራ ያለውን ወንጀል ይናገራሉ።


በየረር ጉሊት የነበሩ ነጋዴዎች በአካባቢው የቆዩበት ዘመን ምናልባትም ወደ ሶስት አስርት አመታት የሚጠጋ ይሆናል ሲሉ የተፈናቃዮቹን ታሪክ ያነሳሉ።


በጀርመን ድልድይ፣በቡራዩ፣በፒያሳና በሌሎች አካባቢዎች የደሃውን የንግድ ቦታ ሲያፈርስ የቆየው አካል ዛሬ ደግሞ በቀጥታ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ነባሩን የየረር ጉሊትን ወደ ፍርስራሽነት መቀየሩን ገልጸዋል።


ንብረቱን እንኳን እንዲያወጣ ጊዜ ያልተሰጠው ነጋዴ አይኑ እያየ ምርቶቹ ከመደብሩ ጋር እንዲፈርሱበት ሆነዋል ይላሉ።


እንደምንም ብለው ንብረታቸውን ያዳኑ ነጋዴዎች ደግሞ ከወረደባቸው ድንገተኛ ዱብ እዳ ጋር ተያይዞ ንብረታቸውን ይዘው ወዴት እንኳን እንደሚሄዱ ግራ ገብቷቸዋል ሲሉ በአካባቢው የነበሩት የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።-ምናልባትም የዚህ የሌባ ስብስብ የሆነው ቡድን ሰለባ ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉም ስጋታቸውን ያስቀምጣሉ።


በየካ፣በሱሉልታና በተለያዩ አካባቢዎች በተለይ የአማራ ተወላጆችን ቤት እያፈረሰ ያለው የኦህዴድ መራሹ ስርአት ባሰማራው ወንጀለኛ ቡድን አማካኝነት የነዋሪውን ንብረት በመስረቅ ተግባር ላይ ተሰማርቷል ብለዋል።


ከዛም አልፎ ቤቱ ፈርሶበት ንብረቱን ለመጫን የሞከረው ነዋሪ ለአፍራሹ ሃይል አስር ሺ ብር አልከፈልክም በሚል ንብረቱ እየተዘረፈበት መሆኑን ኢትዮ 360 በተደጋጋሚ መረጃውን ማውጣቱ ይታወሳል።

Recent Posts

See All

ነሃሴ 18/2015 በሰሜን ሸዋ ሽንፈቱን የተከናነበው የገዳይ ቡድኑ ስብስብ የተረፈውን ሃይሉ ሰብስቦ ወደ አካባቢው መመለሱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።

በሰሜን ሸዋ አንፆኪያ /መኮይ/ ገና በጠዋቱ ሽንፈቱን የተከናነበው የገዳይ ቡድኑ ስብስብ የተረፈውን ሃይሉ ሰብስቦ ወደ አካባቢው መመለሱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ። ገና ሳይነጋ ንጹሃንን ሊፈጅ ወደ በአንጾኪያ አካባቢ ጦርነት ቢከፍትም ከህዝባዊ ሃይሉ ጥይት ግን ሊያመልጥ አልቻለም ብለዋል ምንጮቹ። ህዝባዊ ሃይሉ የ

ነሐሴ 18/2015 የብአዴን አመራሮች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን የኢትዮ ገለጹ።

በሰሜን ሸዋ ደብረብርሃንና አካባቢው መረጃ በመስጠትና መንገድ በመምራት ጭምር ህዝባቸውን እያስጨረሱ ላሉ የብአዴን አመራሮች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ። በማስጠንቀቂያው ላይ በዋናነት በዚህ ክህደት ውስጥ መሪ ተዋናይ የሆኑ አመራሮች ስም ዝርዝርና የሚገኙበት አድራሻ ጭምር ይፋ መሆኑን

ነሐሴ 18/2015 የዶንጋ ማህበረሰብ መብቱን በመጠየቁ ብቻ እየተሳደደና እየታሰረ ነው ሲሉ የማህበረሰቡ አባላት ገለጹ።

በደቡብ ክልል አዲስ ተመሰረተ በተባለው ክልል ውስጥ ያሉው የዶንጋ ማህበረሰብ መብቱን በመጠየቁ ብቻ እየተሳደደና እየታሰረ ነው ሲሉ የማህበረሰቡ አባላት ለኢትዮ 360 ገለጹ። አዲስ ተቋቋመ በተባለውና ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ በተቃወመው ክልል ውስጥ ዛሬ ላይ በርካታ ወጣቶች በገፍ እየታሰሩ መሆኑን አስቀምጠዋል። የተ

Comentarios


bottom of page