አርበኛ ዘመነ ካሴን በግዴታ ችሎት ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
በተደጋጋሚ አርበኛ ዘመነ ካሴ ፍርድ ቤት ቅረብ ለሚለው ጥያቄ የሰጠው የአልቀርብም ምላሽ የኦህዴዱንም ሆነ የብአዴኑን እቅድ ማክሸፉ ይታወቃል።
ከፌደራል ጀምሮ እስከ ክልል በተደጋጋሚ ሲደረግ የነበረውና አርበኛውን በምን መልኩ ማስወገድ ይችላል በሚለው ስብሰባ ላይ አንዱ መንገድ ዘመነን ፍርድ ቤት ማቅረብ የሚል መሆኑን ኢትዮ 360 በመረጃው ማውጣቱ ይታወሳል።
እናም አሁን ላይ ይሄው አካል በዚህ መልኩ ያስቀመጠውን እቅድ ለማሳካት አርበኛ ዘመነን በግዴታ ፍርድ ቤት ለማቅረብ ተዘጋጅቷል ብለዋል።
በዚህ ሂደት ውስጥ ደግሞ ሁከት በመፍጠርና እሱ የፈጠረው በማስመሰል እርምጃ መውሰድ ነው ይላሉ።
ይህን እቅድ ለማሳካትም በግዴታ ፍርድ ቤት ማቅረብ የሚለው ጉዳይ ከስምምነት ላይ ተደርሶበታል ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።
Comments