top of page

ኢትዮ 360-ግንቦት 8/2015) የአማራ ክልል አርሶ አደሮችን እንዳያርሱ የማድረግ የመጨረሻው ደረጃ ተደርሷል።የአማራ ክልል አርሶ አደሮችን እንዳያርሱ የማድ


ለዚህ ማሳያው ደግሞ ትላንት የአፈር ማዳበሪያ ለመጠየቅ አደባባይ የወጣው ብቻ ሳይሆን ሁሉም የክልሉ አርሶ አደር በሚባል ደረጃ አደጋ ላይ ወድቋል ይላሉ።


ምንጮቹ በክልሉ ማዳበሪያ የሚያሰራጩ 23 የህብረት ስራ ማህበራት ቢኖሩም፣ከአንዳቸው መጋዘን ውስጥ ግን ምንም አይነት የማዳበሪያ ምርት እንዳይኖር ተደርጓል ሲሉ ያለውን እውነታ አስቀምጠዋል።


የህብረት ስራ ማህበራቱ ጥያቄያቸውን በተደጋጋሚ ለማንሳት ቢሞክሩም የማዳበሪያን ጉዳይ አታጯጩሁት በሚል እላይ ካለው አካል ማስፈራሪያ እየተሰጣቸው አፋቸውን እንዲዘጉ እየተደረጉ መሆኑን ምንጮቹ አስታውቀዋል።


ሁሉም ማህበራት ከማደበሪያ አቅርቦት ውጪ እንዲሆኑ ሲደረግ ምናልባትም ይሄ በክልሉ ታሪክ የመጀመሪያው ሳይሆን አይቀርም ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ግምታቸውን አስቀምጠዋል።


ቀደም ሲል ማዳበሪያን በሚመለከት አሰራሩ የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን በሚባለዉ ድርጅት አማካኝነት ማዳበሪያ ከዉጭ ቀጥታ ግዥ ፈጽሞ ወደ ክልሎች ማእከላዊ መጋዘን ያደርስ እንደነበር ያነሳሉ።


ይሄ ማለት ደግሞ ቀጥታ ግዥ ከተፈጸመበት አገር በጅቡቲ ወደብ ተጓጉዞ ወደ ክልል የማእከል መጋዘን የሚመጣ ሲሆን በቀጣይ ደግሞ የህብረት ስራ ማህበራት ምርቱን ተቀብለው ወደ ወረዳ የሚያጓጓዙን ስራ ይሰሩ ነበር ብለዋል ፡፡


ዛሬ ግን ያ ሁሉ ነገር ተቀይሮ አማራ ክልል ከኦሮሚያ ክልል የተለያዪ ከተሞች የማዳበሪያ ግዥ ተፈጽሞ በጥቁር አባይ ተጓጉዞ እንዲመጣ በመደረግ ላይ መሆኑን ያጋልጣሉ።


ይሄ ማለት ደግሞ ባለጊዜው የኦህዴዱ አካል ማዳበሪያው ከውጭ ከተገዛበት ሌላ ጭማሪ በማድረግና የማጓጓዣው ሒሳብ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ በማድረግ የሚስተናገድ ሆኗል ይላሉ።


የኦህዴድ መራሹ ስርአት ይሄን የሚያደርገው ደግሞ ክልሉም ሆነ ህብረት ስራ ማህበራቱ ብሎም አርሶ አደሩ የሚጠየቀውን ገንዘብ ከፍለው መግዛት አይችሉም የሚል ድምዳሜ ላይ በመድረሱ ነው ብለዋል።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

bottom of page