በሞጃና ወደራ አካባቢ የሚንቀሳቀሰው የአማራ ህዝባዊ ሃይል ከ3መቶ በላይ የገዳዩን ቡድን ሃይል ከነመሳሪያው ሲማርክ ሞረትና ጁሩ ላይ ደግሞ ህዝባዊ ሃይሉ ገዳዩን ቡድን ከቦ መውጫ እንዲያጣ ማድረጉን የህዝባዊ ሃይሉ አባላት ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ከለሚ ወደ ወደ ኩኬለሽ ሲያመራ የነበረው የገዳዩ ቡድን ቁጥር 305 እንደሚሆን ይናገራሉ።
ይሄንን ቡድን ሲመራና ሲያዋጋ የነበረው የፍኖተ ሰላም ልጅ እንደነበርና እየሰሩ ያሉት ስራ ስህተት መሆኑን ከሌሎች ጋር ሆኖ በማሳመኑ ሙሉ መሳሪያቸውን አስረክበው ህዝባዊ ሃይሉን መቀላቀላቸውን ነው የሚናገሩት።
ሞረትና ጁሩ እነዋሬ እንዲሁም ወገሬ ላይም በተመሳሳይ ህዝባዊ ሃይሉ የገዳዩን ቡድን ከቦ መውጫ አሳጥቶታል ብለዋል።
ከመርሃቤቴና አካባቢው የተሰባሰበው ሃይል ገዳዩን ቡድን መውጫ ሲያሳጠው የመንዝ ማማ ምድር በሆነችው አካባቢም ህዝባዊ ሃይሉ ከገዳይ ቡድኑ ጋር ጦርነት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
መርሃቤቴ ቀጠና ጃማ ዶጎሎ ላይ ደግሞ የሚከፈለው ገንዘብ ከፍ እንዲልለት ለተደረገውና በሚሊሻ ስም ለተሰባሰበው ገዳይ ቡድን ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው መሆኑን ነው አባላቱ የሚናገሩት።
በዚህ አካባቢ ግን ትልቅ ችግር እየፈጠረ ያለው የአካባቢው ተወላጅ የሆነውና ቀጠናውን የሚመራው ሜጄር ጂኔራል መሃመድ ተሰማ ዘመዶቹን ሁሉ አሰባብሶ የመርሃቤቴ አካባቢውን ለመውጋት መነሳቱ ነው ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።
ትላንት ደብረብርሃን ላይ ከየአካባቢው ለተሰባሰበው ነዋሪ በተደረገው ስብሰባ ላይ ማህበረሰቡ በአስቸኳይ ኮማንድ ፖስቱ እንዲነሳ በግልጽ መጠየቃቸውን ተናግረዋል።
ያ ካልሆነ ግን ማህበረሰቡ በራሱ የራሱን አማራጭ ይወስዳል ከማለቱም በላይ ቤተመንግስቱን ለተቆጣጠረው ግለሰብ በቀጥታ የሚደርስ መልእክትን ለሰብሳቢቹ በግልጽ ካስቀመጡ በኋላ ያለ ምንም ስምምነት ስብሰባው እንዲበተን ሆኗል ብለዋል አባላቱ።
Comments