top of page

(ኢትዮ 360 -ጳጉሜ 1/2015) በሰሜን ሸዋ የምንጃር ሸንኮራንና የበረህት አካባቢዎች ወደ ቀድሞ እንቅስቃሴያቸው ተመለሱ።

በሰሜን ሸዋ የምጃር ሸንኮራንና የበረህት አካባቢዎችን የተቆጣጠረው ህዝባዊ ሃይሉ በቀጣይ ሃገረ ማርያምና አሳግርትን በቀጣይ በእጁ እንደሚያስገባ የአማራ ህዝብ ትግል መሪዎች ለኢትዮ 360 ገለጹ።


አሁን ባለው ሁኔታ የምንጃርና ሸንኮራ አካባቢዎችን አፈነግጣለሁ ያለውን ቡድን ጨምሮ ካስወገደ በኋላ አካባቢውን ወደ ቀድሞ እንቅስቃሴው እንዲመለስ ማድረጉን ነው የሚናገሩት።


በዚህ ጦርነት አንድም የህዝባዊ ሃይሉ አባል መጎዳት አይደለም ጭረት እንኳን አላገኘውም ሲሉ የህዝባዊ ሃይሉን ጀግንነት አስምረውበታል።


የበረህትና አካባቢውን ከገዳዩ ቡድን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይልም አካባቢውን ወደ ቀድሞው እንቅስቃሴ እንዲመለስ ማድረጉን ተናግረዋል።


ሃገረማርያምና አሳግርትን ነጻ እንደሚያወጡ የሚናገሩት የትግሉ መሪዎች ለዚህ ደግሞ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ድጋፉን ማድረግ አለበት ሲሉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ በጎጃም የደጋ ዳሞት ሆድ አደር ካድሬዎች የተሳሳቱ መረጃዎችን ለህዝቡ በማሰራጨት ለትግሉ እንቅፋት መሆናቸውን ቀጥለዋል ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።


ነገር ግን አሁን ህዝባዊ ሃይሉ ለነዚህ ሆደ አደር ስብስቦች የመጨረሻውን ማስጠንቀቂያ ሰቷል ይሄን አይተው የማይለመለሱ ከሆነ ደግሞ የጓደኞቻቸው እጣ ፋንታን ያገኛሉ በሚል በግልጽ እንደተነገራቸውም አንስተዋል።


በዚሁ በጎጃም ደብረኤልያስ አካባቢው የገባው የገዳይ ቡድኑ ሃይልም በአማራ ህዝባዊ ሃይል ዋጋውን እያገኘ መሆኑን ነው ምንጮቹ ያመለከቱት።


በሜጫ ከተማ ህጻናትን ሳይቀር በአደባባይ የረሸነው ገዳይ ቡድን አዴት ላይ ከህዝባዊ ሃይሉ በተገቢው መልኩ ሒሳቡን እያገኘ መሆኑን ያነገራሉ።

ከአዴት ተነስቶ ወደ ብራቃት በመጓዝ ላይ የነበረው ገዳይ ቡድን ከአካባቢው አርሶ አደር ድንገተኛ መብረቅ እንደወረደበትም አመልክተዋል።

በቅርብ ርቀት የሚገኘው ህዝባዊ ሃይሉም ይሄንን ገዳይ ቡድን ጥሩ አቀባበል ሊያደርግለት መዘጋጀቱንም ነው ምንጮቹ የተናገሩት።


Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

Comments


bottom of page