top of page

(ኢትዮ 360 -ጳጉሜ 1/2015) በስልጤ ዞን ወደ 5ሺ የሚሆን ነዋሪ ከቀዬው ተፈናቀለ።


በስልጤ ዞን ቀበት ከተማ ትላንት ጽንፈኛ የሙስሊም አክራሪ ቡድን ነኝ የሚለው ስብስብ ከፈጸመው ጥቃት ጋር ተያይዞ ወደ 5ሺ የሚሆን ነዋሪ ከቀዬው መፈናቀሉን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።


ነዋሪዎቹ የትላንቱ ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት ባለፉት ወራት በተደጋጋሚ በክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ ከባድ ወከባ ሲፈጸም መክረሙን ይናገራሉ።


ከዛም ለፎ ሞንታርቦ በማዘጋጀት ጭምር ክርስቲያን ከከተማው እንዲወጣና ሌላው ማህበረሰብም እንዲያፈናቅላቸው ሲቀሰቅሱ መክረማቸውን አንስተዋል።


ከዛም አልፎ የክርስቲያኑን የንግድ ተቋማትም ሆነ የመጓጓዣ አገልግሎትን እንዳይጠቁሙ ቅስቀሳ ሲያደርጉ በወቅቱ በአካባቢው ያለው የጸጥታ ሃይል እንዳስቆማቸውና እንዳሰራቸው ገልጸዋል።


ይሄንን ያየው ጽንፈኛ ቡድን ቀን ጠብቆ ትላንት ሌላ አካል እንዳይደርስላቸው መንገድ በመዝጋት ጭምር ጥቃት መፈጸሙን አስታውቀዋል።


የክርስቲያን ቤት እየተመረጠ ተቃጥሏል፣በድንጋይ ተደብድቧል ከባድ ጉዳትም ደርሷል ብለዋል።

ይሄንን ጥቃት ተከትሎም ወደ 5ሺ የሚሆን ነዋሪው ቀዬውን ለቆ ወደ ቡታጅራና አካባቢው መፈናቀላቸውን ተናግረዋል።


ይሄ ጥቃት ሲፈጸምና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ከርስቲያናትን እናቃጥላለን የሚል እንቅስቃሴ በመኖሩ ካህናቱ በድንጋይ እየተደበደቡ ጭምር ታቦታቱን ለማሸሽ ችለዋል ብለዋል።


ይሄ ሁሉ ሺ ህዝብ ሲፈናቀልና ይሄ ሁሉ ጉዳት ሲደርስ አንድም አካል ግን ዞር ብሎ ሊያያቸው አልቻለም የሚሉት ነዋሪዎቹ ነገር ግን ማህበረሰቡ አንድ ላይ ሆኖ ተፈናቃዮቹን ለመርዳት እየሞከረ መሆኑን ገልጸዋል።


አሁንም ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ንብረታቸው በዚሁ ጽንፈኛ ቡድን እየተዘረፈ መሆኑን ነው ነዋሪዎቹ የሚናገሩት።


ከዛም አልፎ የጸጥታ ሃይሉ መንገድ ከማስከፈት ሌላ ያደረገው አናዳችም ነገር የለም ብለዋል።

አሁን እየሆነ ያለው የብሔር ጉዳይ ሳይሆን ክርስቲያንን የማጥፋት አጀንዳ ነው ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።


Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

Σχόλια


bottom of page