በጋምቤላ ማጃንግ ዞን ጎደሬ ወረዳ በአማራ ተወላጆች ላይ የተጀመረው ጥቃት ዛሬም ተጠናክሮ መቀጠሉን የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጹ።
በዚህ ጥቃት እስካሁን ሰባት ሰዎች መገደላቸው ቢታወቅም ነገር ግን ጥቃቱ በተለያዩ አካባቢዎች ከመፈጸሙ ጋር ተያይዞ የሟቾቹ ቁጥር ከዚህም በላይ ሊጨምር እንደሚችልም አመልክተዋል።
ከዚህ ጥቃት ጋር ተያይዞ በርካታ የአማራ ተወላጆች ከመጎዳታቸው ጋር ተያይዞም የተጎጂዎቹን ቁጥር በትክክል ማወቅ አለመቻሉንም ምንጮቹ ገልጸዋል።
በተደጋጋሚ በክልሉ የሚፈጸመው ይሄንን አይነቱን ጥቃት የትኛውም አካል ሊያስቆመው ባለመቻሉ አሁንም በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጸመው ግድያ ቀጥሏል ሲሉ ምንጮቹ ተናግረዋል።
Kommentare