(
በአዲስ አበባ በሙሉ ነጋዴዎችን እና የመንግስት ሰራተኞችን ለመስቀል በአል መከላከያዎችን በሬ እናብላ በሚል እያዋከቡት መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
ነጋዴውንና የመንግስት ሰራተኛውን በዚህ መልኩ ቢያዋክቡትም ህብረተሰቡ ግን በዚህ ኑሮ ውድነት ሽንኩርት 95 ብር ጤፍ አንድ ኪሎ 120 ብር፣ፓስታ 80 ብር፣ ሩዝ 90ብር፣ መኮረኒ 120ብር በሆነበትና ለጆቻችንን አንድ ዳቦ ገዝተን ማብላት ባልቻልንበት ሁኔታ ውስጥ ምንም አትጠይቁን የሚል ክርር ያለ ምላሽ እየተሰጣቸው መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
መከላከያ የራሱ በጀት አለው ለዚያውም አገሪቱ የምትበጅተው አንደኛ የመከላከያ ሁለተኛ የጤና ሶስተኛ የትምህርት ነው ስለዚህ ምን አርጉነው የምትሉን በማለት በየቦታው አሳፍረው መልሰዋቸዋል ብለዋል።
የወረዳ ካድሬዎች በጠሩት ስብስበ ላይ የሰራተኛውንና የነጋዴውን ተወካዮች ከደሞዝ ነው የምቆርጠው ያ ደግሞ ችግር የለውም የሚል ነገር በማንሳት ለማግባባት ቢሞክሩም በፍጹም የማይቻል ነገር ነው በሚል ቁርጥ ያለ ምላሽ እንደሰጧቸውም ተናግረዋል።
አሁን ላይ ያለው ሁኔታ እንኳን ብር አዋጡ የሚባልበት ሳይሆን ህዝቡ በረሃብ አደባባይ ሊወጣ የተዘጋጀበት ነው ሲሉ ቁርጡን እንደነበገሯቸውም ምንጮቹ አመልክተዋል።
ስብስባ የተጠራችሁት ሔዳችሁ ሌላውን እንድታሳምኑ እንጂ ሌላ አመጽ እንድትቀሰቅሱ አይደለም በሚል ሊያስፈራሩ ቢሞክሩም እኛ ተወክለን እንምጣ እንጂ እኛም የዚህ ችግር ሰለባ ነን በሚል ምላሽ መስጠታቸውን ተከትሎ ስብሰባው ያለምንም ውጤት መጠናቀቁን ነው የተናገሩት።
Comments