በጎንደር ጯሂት አካባቢን ጨምሮ በተለያዩ የጎንደር አካባቢዎች የሰው በላይ ስርአት ሃይል በከባድ ሁኔታ ሽንፈት መከናነቡን የህዝባዊ ሃይል አባላቱ የኢትዮ 360 ገልጸዋል።
በጩሂት አካባቢ በንጹሃን ላይ ጦርነት የከፈተው ገዳይ ቡዳን አይቀጡ ቅጣት ተቀጦ የተረፈው ሙሉ በሙሉ እግሬ አውጭኝ ብሎ እየፈረጠጠ መሆኑን ነው የሚናገሩት።
የቆላ ዳባ ከተማን ከዚሁ ገዳይ ቡድን ሙሉ በሙሉ ነጻ መውጣቱ ታውቋል።
ሆድ አድሩ አድማ ብተና የሚባል ቡድን ደግሞ ከአካባቢው እንዲያስወጡት እየተማጸነ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
በግራኝ በር ወደ በለሳ መውሰጃ ላይም ከአካባቢው ሸሽቶ የነበረውን ቡድን በሽምቅ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው ህዝባዊ ሃይሉ የበላይነትን ተቆጣጥረውዋል።
የህዝባዊ ሃይሉ አባላት ከየአካባቢው ባሰባሰቡት መረጃም በዚህ ጦርነት የጄኔራል ማዕረግ ያለው የገዳዩ ቡድን ጦር መሪ መገደሉን የሚያበስር መረጃ መስማታቸውንም ይናገራሉ።
ከውስጥ ምንጮቻቸው ባሰባሰቡት መረጃ መሰረትም በዚህ ቦታ በተደረገው ውጊያ ከገዳዩ ቡድንና አድማ ብተና ከሚባለው ስብስብ እስከ 300 የሚደርስ ሃይል ሙትና ቁስለኛ እንደተደረገ ማወቃቸውንም ገልጸዋል።
Comments