የአዲሥ አበባ ከተማን ሕዝብ ኑሮ የበለጠ የሚያከብድ የቤት ኪራይ ጭማሪ መደረጉን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
ይሄው የሰው በላ ስብስብ ደሃው የከተማ ህዝብ በአብዛኛው የሚኖርበትን የቀበሌ ቤቶች ኪራይ ላይም ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ ማድረጉንም ይናገራሉ።
አረመኔው የኦነግ ብልጽግና የአቢይ መንግሥት በደርግ ሥርአት በተወረሱ የቀበሌ ቤቶች ላይ ነው ጭማሪውን ያደረገው።
በየትኛውም መገናኛ ብዙሃን ሳይገጽ በአዳነች አበቤ ትእዛዝ ብቻ የተተገበረው ይሕ ጭማሪ ቀድሞ ይከፈል ከነበረው ከሶስት እሥከ አራት እጥፍ እንዲጨመር መደረጉንም ምንጮቹ ኪራይ ለመክፈል የሄዱ ነዋሪዎች አናግረው ያገኙትን መረጃ ገልጸዋል።
በደርግ ሥርአት ተተምኖ በኢሕአዴግ ሥርአትም የቀጠለው የቀበሌ የቤት ኪራይ ላይ ጭማሪ የተደረገው አንድም ደሃውን የሕብረተሰብ ክፍል ለመጉዳትና የኑሮ ውድነቱን በማባባስ የአዲሥ አበባ ከተማን ሕዝብ ለመበቀል የታቀደ ተግባር ነው ሲሉ እውነታውን አስቀምጠዋል።
ቀድሞ 8 ብር ይከፈል ለነበረ ደሳሳ ጎጆ 40 ብር 20 ብር ይከፈል ለነበረ የፈራረሰ ጭቃ ቤት 100ብርና ከዚያ በላይ እንዲከፍሉ እየተገደዱ ያሉት በወር 30 ብር ጡረታ የሚያገኙና በየጎዳናው እየተባረሩ ሻይቡና የሚሸጡ እናቶች መሆናቸው ደግሞ ነገሩን አክብዶታል።
ከደርግ ጊዜ ጀምሮ በአዲስ አበባ በወር ከሃምሳ ሳንቲም ጀምሮ የቀበሌ የቤት ኪራይ እየከፈሉ ይኖሩ የነበሩ የአካል ጉዳተኞችና አቅመ ደካሞች በጭማሪ ሽፋን ጎዳና ሊጣሉና ቤትና ቦታቸውን ለባለጊዜዎች ለመሥጠት ተተሸረበ ሌላኛው ሴራ ነው ሲሉም አጋልጠዋል።
አሁን ላይ በግልጽ እነዚህ ደሃ የሚባሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ኪራዩን ማስከፈል መጀመራቸውንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
የአዲስ አበባን ሕዝብ በማፈን፣ ቤቱን አፍርሶ በማፈናቀል፣ በማሰር፣ ያልረካው የሰው በላው ስብስብ አሁን ደግሞ የከተማውን ህዝብ በረሃብ ሊፈጀው ተዘጋጅቷል ሲሉም ያለውን ሁኔታ አስቀምጠዋል።
ነገር ግን ምናልባትም የጨካኙ ስርአት አካሄድ የከተማዋን ህዝብ ለማያዳግም ትግል እንዲነሳና ይሄንን ጨካኝ ስርአት ገርስሶ እንዲጥል እያነሳሳው ነው ሲሉም ሁኔታውን ገልጸዋል።