የቀድሞ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሃላፊ የነበረችው ብርቱካን ሚደቅሳ የግል ጠባቂ ከነሙሉ ትጥቁ መጥፋቱን ተከትሎ ከባድ ውጥረት መንገሱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
ካርል አደባባይ አካባቢ ካለው መኖሪያ ቤቷ ከነሙሉ ትጥቁ የተሰወረውን ጠባቂዋን መጥፋት ተከትሎ ፌደራል ፖሊስ ላይ አመራሮች ናቸው የሚባሉ ስብስቦች ቤቱ ውስጥ ፍተሻ በማድረግ ስራ መወጠራቸውን ተናግረዋል።
በቪ8 ተሽከርካሪ በአጃቢ የምትመላለሰው ወይዘሪት ብርቱካን አሉዋት ከሚባሉት ጠባቂዎቿ አንዱ ይሄ ከነመሳሪያው የጠፋውና የአማራ ተወላጅ የሆነው ጠባቂዋ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
የዚህ ጠባቂ መጥፋት ብዙ ሚስጥሮችን እንዲወጣ ሊያደርግ ይችላል ብሎ የፈራው የሰው በላስ ስብስብ አሁንም ጠባቂው የገባበትን ለማወቅ ከባድ ምርመራ እያደረገ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
Comments