በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የህዋት ደጋፊ፣ ባለሃብትና ካድሬዎች በሰሜኑ ጦርነት የተሳተፉ የአማራ ተወላጆችን በመጠቆምና በማሳፈን ላይ መሆናቸውን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
በከተማዋ ነዋሪ ከሆኑትም ሌላ በእርቅ ሰበብ ወደ አዲስ አበባ ከተማ የገቡ የህወሃት ካድሬ፣ደጋፊና ባለሃብት የፋኖ ህዝባዊ አባላት ያሏቸውንና ማህበረሰብ አንቂዎች ናቸው በሚል በነሱ ስያሜ ያገኙትን ሁሉ በማሳፈን ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ይሄንን አፈና በግልጽ እያካሄዱ ያሉት ደግሞ ከኦህዴዱ አፋኝ ቡድን ጋር በጋራ በመሆን ነው ሲሉ ምንጮቹ አስታውቀዋል።
አሁን ላይ የአማራውን ተወላጅ እያስጠቆሙ የሚያሳስቱ የህወሃት ደጋፊ፣ካድሬና ባለሃብቶችን ስም ዝርዝር ኢትዮ 360 በቅርቡ ለህዝቡ ይፋ የሚያደርገውም ይሆናል።
የህወሃቱ ጥቆማ ያለበቃውና ሸገር የሚል የዳቦ ስም በመስጠት የነዋሪውን ቤት አፍርሶ ያልጨረሰው ህገወጡ ስብስብ ደግሞ ሌላ መመሪያ ማውረዱን ይናገራሉ።
ይሄም መመሪያ በአካባቢው ቤቱ ሳይፈርስ በአካባቢው የቀረና ለስርአቱ አደጋ ነው የተባለ የአማራ ተወላጅን ለጠቆመ 15ሺ ብር ይከፈለዋል የሚል መሆኑን ያነሳሉ።
አሁን ላይ በሁሉም አቅጣጫ አደጋ የተደቀነበት የአማራ ተወላጅን ለማስመታት ደግሞ ሆድ አደሩ ካድሬ ሌት ተቀን እየለፋ ነው ሲሉ ምንጮቹ ተናግረዋል።