በአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤት ኮንዶሚኒየሙን ለሚሸጥ ነዋሪ አዲስ የስም ማዛወሪያ ታሪፍ መውጣቱን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።
ከዚህ በፊት ይላሉ ምንጮቹ አንድ የከተማዋ ነዋሪ የኮንዶሚኒየም ቤቱን ሲሸጥ ለስም ማዛወሪያ የሚከፍለው ቢበዛ ሃያ ሺ ብር ብቻ እንደነበር ይናገራሉ።
አሁን ግን አዲሱ የአዳነች አበቤ የሌብነት መንገድ ቤቱን የሚሸጥ ሰው የሚከፍለው በካሬ ሜትር በሚወጣለት ተመን ልክ ነው የሚል አዲስ የዘረፋ መመሪያ ይፋ መሆኑን አመልክተዋል።
በካሬ ሂሳብ የወጣለት ነዋሪውም የጋራ መኖሪያ ቤቱን በርካሽ ቢሸጥም የሚከፍለዉ የስም ማዛወሪያ ሒሳብ ግን እሷ ባወጣችዉ ዋጋ ነዉ ይላሉ።
በማሳያነትም ለ29 ካሬ ስም ማዛወሪያ ሰባ አምስት ሽህ ብር መክፈል ይጠበቅበታል ብለዋል።
ካሬዉ ሲጨምር ደግሞ የክፍያው መጠንም በዛው መጠን እየጨመረ ይሄዳል ሲሉ በነ አዳነች አበቤ የወጣውን አዲሱን ህዝብን የመዝረፊያና የማማረሪያ መንገድን ያስቀምጣሉ።
መኖርም ንብረቱን መሸጥም ካልተፈቀደለት የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ በአመት ምን ያህል ገቢ ማግኘት ይቻላል የሚለውም አስቀድሞ የተሰራ አጀንዳ መሆኑንም አስታውሰዋል።