የአማራ ተማሪዎች ማህበር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዮናስ ገብሬ በአፋኙ ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ መታፈኑን የማህበሩ ፕሬዝዳንት ወጣት ኤርሚያስ ጥጋቤ አስታወቀ።
የጽህፈት ቤት ሃላፊው ዮናስ ገብሬ ተቋማዊ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቶ ከደብረ ማርቆስ ወደ ባህርዳር በመመለስ ላይ ባለበት ወቅት መታፈኑን ያናገራሉ።
ከተሳፈረበት ተሽከርካሪ አስወርዶ ያፈነው ቡድን በደብረ ማርቆስ ከተማ ወደ ሚገኘው አራተኛ (4ኛ) ፓሊስ ጣቢያ እንደወሰደውም ፕሬዝዳንቱ አስታውቋል።
የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) አሁን እየተሰራ ባለው ስራ ይህን ስርዓት ከማውገዝ ባለፈ ዛሬም እንደ ትናንቱ ለመታገል ዝግጁ ነን ሲሉም በፕሬዛንታቸው በኩል ለመላው የአማራ ሕዝብ መልዕክታቸውን አስተላለፈዋል።
ዮናስ ገብሬን ዛሬ ያፈነው አካል የማህበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት ሲሳይ መልካሙንም አፍኖ በማሰቃየት ላይ መሆኑንም በመረጃው ላይ አመልክቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ ከተለያዩአ ካባቢዎች ታፍነው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ የተደረጉት የአማራ ተወላጆች ዋስትና ቢፈቀድላቸውን የያዛቸው አካል ግን ሊለቃቸው ፈቃደኛ አለመሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።
በተለይ በነመላከምሳሌ የክስ መዝገብ የተከሠሡ 28 ሠዎች በሠላሣና በሀያሽብር ዋሥ እዴፈቱ መወሰኑን ተናግረዋል።
ነገር ግን ፍርድ ቤቱ ይሄን ውሳኔ ያሳልፍ እንጂ አፋኙ ቡድን ግን ችሎት እንኳን እንዳይቀርቡ አድርጎ እንደወሰዳቸው ምንጮቹ አመልክተዋል።
ቤተሰቦቻቸውና ጓደኞቻቸው በተደጋጋሚ አቤት ለማለት ቢሞክሩም እስካሁን ግን ምላሽ የሚሰጣቸው አካል ግን ማግኘት እንዳልቻሉ ነው የሚናገሩት።
Comentários