top of page

(ኢትዮ 360_ሰኔ 21/2015) የዒድ አል አድሃ (አረፋ) 1 ሺህ 444ኛው በዓል ተከበረ።


የዒድ አል አድሃ (አረፋ) 1 ሺህ 444ኛው በዓል በአዲስ አበባና በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነስርአቶች ተከብሮ ዋለ።


በአሉ በአዲስ አበባ ከተማና በተለያዩ አካባቢች የተቸገሩትን በመርዳትና በተለያዩ ስነስርአቶች መከበሩን የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ በኮምቦልቻ ከተማ ህዝበ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ኢድን ኻሊድ መስጅድ እንዳይሰግድ በአስለቃሽ ጭስ እንዲበተን መደረጉን ምንጮቹ ተናገረዋል።


ነገር ግን ህዝበ ሙስሊሙን በአስለቃሽ ጭስ የበተነው አካል በኡመር መስጅድ ስግደቱን እንዳያካሂድ ግን ማድረግ አልቻለም ብለዋል።


የኦህዴዱ ስርአት እኔ በመረጥኩላቹህ መጅሊስ ተመሩ ከእኔ ትእዛዝ መውጣት አትችሉም ለማለት ቢሞክርም ሊሳካለት ግን አልቻለም ብለዋል።


ይሄ ሁሉ ያልተሳካለት ስብስብ በአሉ ከመካሄዱ ከቀናት በፊት ጀምሮ ታላላቅ ኡለሞችን እና አባቶችን ሲያስር መሰንበቱንም የኢትዮ 360 ምንጮች አስታውሰዋል።


ይሄንን እያደረገ ያለው ደግሞ የከተማው ከንቲባ ከኦህዴዱ ሃይልና ከሌሎች ካድሬዎች ጋር መሆኑን ነው ሲሉም ያጋልጣሉ።


በህዝብ ያልተመረጡ አካላትን መጅሊስ ላይ እሾማለሁ በሚል ያለውን አቅም ሁሉ እየተጠቀመ ያለው ይሄው ስብስብ በወሎ ኮምቦልቻ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከ50 እስከ 85 አመት እድሜያቸው የሚደርስ አዛውንቶችንና ኡለሞች ላወያያችሁ በሚል የእስር ዘመቻ ከፍቶባቸዋል ብለዋል።


እስካሁንም የ85 አመቱን የእድሜ ባለጸጋ ሼህ ሙሐመድ ሱሩር ሱለይማንን፣ የ75 አመቱን ሼህ ሐሰን ይመርን፣ የ70 አመቱን ሸህ ዩሱፍ አሊን ጨምሮ በርካታ የእምነቱ አባቶችም በዚሁ ቡድን በስብሰባ ሰበብ መታፈናቸውን የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።



Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

Comments


bottom of page