በድሬደዋ የሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች የአብይ አህመድን የመደመር መጽሃፍ በ1ሺ ብር እንዲገዙ መገደዳቸውን ለኢትዮ 360 ገለጹ።
በተለይ የድሬደዋ ሪፈራል ሆስፒታል ባለሙያዎች መጽሃፉን አንገዛም በሚል በግልጽ አቋማቸውን ቢያሳውቁም ነገር ግን በግዴታ ከደሞዛችሁ የቆረጣል በሚል ወረቀት ፈርሙ መባላቸውን ያነሳሉ።
ሰሞኑን መጽሃፉን በ700 ብር እንዲገዙ መምህራንን ሲያስገድድ የነበረው ስብስብ በቀናት ልዩነት የመጽሃፉን ዋጋ አንድ ሺ ብር አስገብቶታል ሲሉ ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አስፍረዋል።
የሪፈራል ሆስፒታሉን ባለሙያዎችና ሰራተኞች ትላንት አስቸኳይ ስብስባ ብሎ የጠራው አካል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መጽሃፉን ትገዛላችሁ፣ይሄም ደግሞ ከደሞዛችሁ ይቆረጣል የሚል አምባገነናዊ ውሳኔ ማሳለፉን ተናግረዋል።
በድሬደዋ የመንግስትና የግል ተቋማት ሰራተኞችን ብር ለመዝረፍ አሰፍስፎ የተነሳው ይሄው አካል በቀጣይ የከተማዋን ነዋሪ ንብረትና ሃብት አልባ ለማድረግ አሰፍስፏል ሲሉም ባለሙያዎቹ በመረጃቸው ላይ አስፍረዋል።