top of page

ኢትዮ 360_ግንቦት 30/2015) በአማራ ክልል ህብረተሰቡን ያነቃሉና የፋኖ ህዝባዊ ሃይልን ይደግፋሉ የሚባሉ ባለሃብቶችና ነዋሪዎች በገፍ እየታፈኑ ነው።


በአማራ ክልል ህብረተሰቡን ያነቃሉና የፋኖ ህዝባዊ ሃይልን ይደግፋሉ የሚባሉ ባለሃብቶችና ነዋሪዎች በገፍ እየታፈኑ መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ለኢትዮ 360 ገለጹ።


ባለሃብቱና ህብረተሰቡን በማንቃትና ችግሮችን በመርዳት የሚታወቁት ባለሃብትና ምሁሩ አቶ ፈሩ ታዬ በዚሁ አፋኝ ቡድን የታፈኑት ሰሞኑን መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ይናገራሉ።


ከአንድ ሺ በላይ የተቸገሩ ህጻናትን በማሳደግ የሚታወቁት አቶ ፈሩ ታዬ ከታፈኑ በሁዋላ ያሉበት ሁኔታም እንደማይታወቅ ነው የገለጹት።


ደብረታቦር ላይ አቦ ከዘራነው የሚባል ወንድማቸው የታፈነባቸው ቤተሰቦች ወገናቸው ከታፈነ አንድ አመት ከአራት ወር ቢያልፈውም ተመልካች ግን ሊያገኝ አልቻለም ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።


ባለቤቱና ልጆቹ የአካል ጉዳተኞች እንደሆኑ የሚናገሩት ቤተሰቦቹ ይሄ እየታየ ፋኖን ትደግፋለን በሚል ብቻ ታፍኗል ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።


ወልዲያ ካፈራቻቸው ጀግኖች አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት ዘውዱ ገበያውም በዚሁ አፋኝ ቡድን ሰሞኑን ወዳልታወቀ ስፍራ ከተወሰዱት መካከል መሆኑን ጓደኞቹ ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አስፍረዋል።


በህወሃት ወረራ ወቅት ከትግል ጓደኞቹ ጋር ትልቅ ተጋድሎ እንዳደረገ የሚነገርለት ዘውዱ ገበያው ከነ አርበኛ ሙሀመድ ቢሆነኝ የዶሌሮቃን የጥላት ምሽግ ሰብረው ሲሰው እሱ ደግሞ ቆስሎ ደሴ ሆስፒታል መግባቱን ያነሳሉ ።

ነገር ግን ከወራት በኋላ ከወራት የወያኔ ጦር ደሴ ከተማን ለመውረር ከበባ ውስጥ ማስገባቱን ሲሰማ ቁስለኞችን ወደ ደብረ ብርሐን ሆስፒታል ሲያጓጉዙ ዙውዱ ግን አልሄድም ደህና ነኝ ውጊያ እገባለሁ ብሎ ቦሩ ስላሴ ላይ ከወያኔ ጦር በቅርብ እርቀት እየተያዩ የሞት ሽረት ትግል ካደረጉት ጀግኖች አንዱ መሆኑንም ይናገራሉ ።


በዚህ ጦርነትም በርካታ ጓዶቹ ሲሰው እሱ በድጋሚ ቆስሎ በሞት እና ህይወት መካከል ሆኖ ደብረ ብርሀን ሆስፒታል መግባቱን ያስታውሳሉ።


ዘውዱ ገበያው አሁንም ወደ ሆስፒታል በመመላለስ ህክምናውን እየተከታተለ ባለበት ሁኔታ ውስጥ ሲቪል በለበሱና የጸጥታው ግብረ ሃይልን ነን ብሎ ራሱን በሚጠራው ቡድን ከቤቱ በር ላይ ታፍኖ መወሰዱን ጓደኞቹ ይናገራሉ።


ነገር ግን ይሄው ቡድን በወቅቱ አፍኖ ሊወስደው ሲል ከፍተኛ ትግል በማድረጉ አንገቱ ላይ መርፌ በመውጋት ጭምር ህክምናውን ሳይጨርስ ወዳልታወቀ ስፍራ እንደወሰዱት ነው የሚናገሩት።


በተመሳሳይ በአዲስ አበባም አፈናው ተጠናክሮ መቀጠሉን የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።


በተለይ ፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ ያለምንም ወንጀላቸው የሚታፈኑ ወጣቶች ቁጥር ከፍተኛ እየሆነ መምጣቱንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


በከፍተኛ ሁኔታ ለወጣቱ መታፈን ምክንያት የሆነችው ደግሞ ብዙነሽ ባዬ ተበጀ የተባለች የአካባቢው ተወላጅ መሆኗን ይናገራሉ።


አብሮ አደግ ጓደኞቿን በማሳፈኗ አንድ የቀበሌ ቤትና በዛው በቀበሌ ውስጥ የስራ እድል በስጦታ የተበረከተላት ብሎም ምንም አይነት መረጃ የሌለው ዲግሪ እንድትይዝ የተደረገችው የ7ኛ ክፍሏ በዙነሽ ባዬ አሁንም ወጣቱን በጥቆማ በገፍ እያሳፈነችው መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል።


በአካባቢው የሚታፈኑ ወጣቶች ጥቆማ በብዙነሽ በኩል ይካሄድ እንጂ ከእሷ ጋር ሆነው ወጣቱን እያስመቱ ያሉ ሆድ አድር የአካባቢው ነዋሪዎች መኖራቸውንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

Comments


bottom of page