የቀድሞ የኢትዮጵያ የሃገር መከላከያ እና ፖሊስ ሰራዊት ማህበር የአማራ ልዩ ሃይልን በሃይል ትጥቅ ለማስፈታት የሚደረገውን ሙከራ አጥብቆ እንደሚቃወም አስታወቀ።
ጊዜ ወስዶ በመነጋገር መፍትሄ ማምጣት ሲቻል መንግስት በሃይል ጉዳዩን ለማስፈጸም የሄደበት መንገድ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ነው ብሏል ለኢትዮ 360 በላከው መግለጫው።
የአማራ ህዝብ ሃገርን በነጻነት ለማቆየት ብርቱ ዋጋ የከፈለ፣በሃገር ግንባታ ታሪክ ውስጥም ጉልህ ስፍራ ያለውን ብሎም ኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነቷ አደጋ ላይ በወደቀ ጊዜ ሁሉ ፈጥኖ በመድረስ ሃገርና ህዝብን የሚታደግ ታላቅ ህዝብ ነው ሲልም ገልጾታል።
ስለዚህም በሰውና በንብረት ላይ አሳዛኝ ጥፋት ከመድረሱ በፊት ተኩስ በማቆም አማራው አለብኝ ለሚለው የህልውና ስጋት መፍትሄ ለማበጀት የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት እንዲደረግ አስቸኳይ ጥሪውን አቅርቧል።