top of page

ግንቦት 10/2015 በአዲስ አበባ የሚታፈኑ ልጆቻቸውን ቤተሰቦቻቸው ማግኘት አልቻሉም።



በአዲስ አበባ ከተለያዩ አካባቢዎች የሚታፈኑ የአማራና የደቡብ ብሔር ተወላጆች ከተያዙ በኋላ ሊያገኟቸው አለመቻላቸውን ቤተሰቦቻቸው ገለጹ።



አፈናውን የሚያካሂዱት ሰዎች ወዴት እንደሚወስዷቸው ቢጠይቁ እንኳን ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ አይደሉም ይላሉ።



ከዛም አልፎ እንደ ኤርሚያስ መኩሪያ አይነቶቹን ለበጎ ተግባር ሲንቀሳቀሱ በገዛ መኪናቸው የታፈኑትን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራና የደቡብ ተወላጆች በዚሁ አፋኝ ቡድን መታገታቸውን ኢትዮ 360 በተደጋጋሚ ምዘገቡ ይታወሳል።



በሸገር ትራንስፖርት ቃሊቲ ዲፖ ቢሮ በእቃ ግዢ ሙያ የተሰማራው እንዳልካቸው እሸቱም የዚህ ቡድን ሰለባ ከሆነ 11 ቀን አልፎታል ብለዋል ባለቤቱ።



በወቅቱ የሚወሰድበትን ቦታ ቢጠይቁም ምላሽ ሲያጡ በሁሉም አቅጣጫ ለማግኘት ሙከራ ማድረጋቸውን ነው የሚያነሱት።



እንዳልካቸው እሸቱ ከታሰረ በኋላ እዚህ ይሆናል ብለው ከመጠራጠር ያለፈ ምንም ፍንጭ ሊያገኙ አለመቻላቸውንም ይናገራሉ።




በየትኛውም ፖለቲካ ውስጥ ምንም አይነት ተሳትፎ የለውም የሚሉት ባለቤቱ ቤቱን እንኳን ሲፈትሹ ያገኙት አንዳችም ነገር የለም ሲሉ በሐዘኔታ ይናገራሉ።


በወቅቱ ከታፈነ በኋላ ስልኩ ላይ ደጋግመው በመደወል ለማግኘት ቢሞክሩም ስልኩ እስከተዘጋበት ጊዜ ድረስ ምላሽ የሚሰጣቸው አካል አለማግኘታቸውም ይናገራሉ።



በጭለማ የታፈነውን እንዳልካቸው እሸቱ የት እንደወሰዱት ማግኘት ያልቻሉት ቤተሰቦቹ አሁንም አፍኖ የወሰደው አካል ያለበትን ቦታ እንዲነግራቸው በመልፋት ላይ መሆናቸውንም ነው ለኢትዮ 360 የገለጹት።


Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

Comments


bottom of page