ብልጽግና የሚባለው አካል ከመጣ ጀምሮ የፈረሱ መስጅዶች ቁጥር ወደ 50 ሊደርስ እንደሚል ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ የእምነቱ ተከታዮች ለኢትዮ 360 ገለጹ።
እነሱ እንደሚሉት ትላንት ብቻ አምስት መስኪዶች ወደ ፍርስራሽነት ተቀይረዋል።
በልጽግናው ያስቀመጠው መጅሊስ በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ በማውጣት ይቅርታ እንዲጠይቅና መስጅዶችን ማፍረስ እንዲያቆም ቢጠይቅም ያ ግን ሊሆን አልቻለም ይላሉ።
የፉሪው ሃምዛ መስጅድን ጨምሮ እስካሁን በዚሁ ቡድን የፍረሱት በስጅዶች ቁጥር ወደ 50 ሊደርስ ይችላል ሲሉም ያነገራሉ።
እሄ እንዳይታወቅ ህዝቡም መረጃ እንዳይኖረው ለማድረግ ደግሞ በሁሉም አቅጣጫ መረጃው እንዲታፈን ተደርጓል ባይ ናቸው።
የመገናኛ ብዙሃን ብቻ ሳይሆን ብልጽግናው ራሱ የሾማቸው የአዲሱ መጅሊስ ሰዎችም ወደ አአካባቢው ሔደው ጉዳዩን እንዳያዩ መከልከላቸውን በግልጽ ተናግረዋል ይላሉ።
ነገር ግን ይሄ ሁሉ ውድመት እየደረሰ ያለው ግን ብልጽግናው በሾመው መጅሊስ እውቅና ሰጭነት ሳይሆን አይቀርም ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።
ይቅርታ ይጠይቅ የተባለው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ይቅርታ መጠየቅ ሳይሆን የሚፈርሱ መስጅዶችን ቁጥር ወደ መጨመርና ተቆርቋሪዎችን ወደ ማሰርና መግደል ነው የሔደው ሲሉም ሁኔታውን ገልጸውታል።
መስጅዶችን ማፍረስ ብቻ ሳይሆን ተከታዩን ከአካባቢው እንዲርቅ በማድረግ ተከታይ ማሳጣት በሚለው የኦህዴዱ ብልጽግና አጀንዳ ነው ሲሉም ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።
ድምጽ
Comments