በኦሮሚያ ክልል ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ አካባቢ ምናሬ ከተማ በሚገኘው የመከላከያ ሃይል ላይ የኦነግ ገዳይ ቡድን በፈጸመው ጥቃት ከ150 በላይ የመከላከያ አባላት መገደላቸው የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
ይሄ ቡድን ጥቃቱን የፈጸመው ድንገተኛ ከበባ በማድረግ መሆኑንም ምንጮቹ ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ይሄ ቡድን ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የመከላከያ ሃይል ከገደለ በኋላ ዲሽቃ መትረየስን ጨምሮ ከባድ መሳሪያዎችን መዝረፉንም ይናገራሉ።
ድንገት ከቦ የጨረሰውን የመከላከያ ሃይል የለበሰውን ወታደራዊ ልብስ ገፎ መውሰዱንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ይሄ ግድያ ከተፈጸመ በኋላም የኦነጉ ገዳይ ቡድን የመከላከያ ሃይሉ አባላቱ አስከሬን እንዳይነሳ ማድረጉንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
አስቀድሞ ወደ አዲስ አበባ እየመጣሁ ነው ሲል ሲዝት የቆየው ይሄ ገዳይ ቡድን አሁንም ጉዞውን ወደ አዲስ አበባ እያደርገ መሆኑንም በግልጽ መናገር ጀምሯል ብለዋል።
በተለያየ አቅጣጫ ከአዲስ አበባ በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሃይሉን እያደራጀ ያለው ይሄ ገዳይ ቡድን እንዲህ አይነቱን ጥቃት በመከላከያ ሃይል ላይ ሲፈጽም መረጃው ሙሉ በሙሉ የሚደርሰው ከላይ ካለው የመከላከያ አዛዦች መሆኑንም ያነሳሉ።
በየአካባቢው በዚህ መልኩ እንዲያልቅ እየተደረገ ያለው የመከላከያ ሃይል በዋናነት ጥቃት የሚፈጸምበትም በራሱ አዛዦች መረጃ ሰጭነትና መንገድ መሪነት መሆኑን ኢትዮ 360 በተደጋጋሚ በመረጃው ሲያወጣ መቆየቱ ይታወሳል።