top of page

ግንቦት 17/2015 በሆሮጉድሩ ወለጋ በጃርዴጋና አካባቢው ለስራ ከሄዱ የአማራ ተወላጅ የሆኑ አባላት መታነፋቸው ታወቀ!


በሆሮጉድሩ ወለጋ በጃርዴጋና አካባቢው ለስራ ከሄዱ የመከላከያ አባላት መካከል የአማራ ተወላጅ የሆኑ የሰራዊቱ አባላት ተለይተው መታፋናቸውን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።በቁጥር ምን ያህል እንደሆነ ማወቅ አልተቻለም የሚሉት ምንጮቹ ነገር ግን ወደ አካባቢው እንዲገባ ተደርጎ የነበረው ሃይል ቁጥሩ ከፍተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የታፋኞቹም ብዛት ከፍተኛ ሊሆን ይችላል ሲሉም ግምታቸውን አስቀምጠዋል።ከዚሁ ሃይል ጋር አብረው የነበሩና የትግል ጓደኞቻቸው ላይ ጥቆማ በመስጠት አፈናው እንዲካሄድ ያደረጉት የኦህዴዱ የመከላከያ አባላት ደግሞ ከነትጥቃቸው ወደ ኦነጉ ቡድን መግባታቸውን ሳይጠቁሙ አላለፉም።በዚሁ ገዳይ ቡድን የታፈኑትና ወዳልታወቀ ስፍራ የተወሰዱት የአማራ ተወላጅ የሆኑት የሰራዊቱ አባላት እስካሁን በህይወት ስለመኖራቸው የታወቀ ነገር የለም ሲሉ ምንጮቹ ተናግረዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚሁ ዞን አሙሩ ወረዳና አካባቢው በየቀኑ በአማራ ተወላጆች ላይ የሚካሄደው አፈና ተጠናክሮ መቀጠሉን የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።ሰሞኑን ብቻ ከየአካባቢው የሚታፈኑ የአማራ ተወላጆች ቁጥር ከፍተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ምን ያህል ለሚለው ምላሽ ማግኘት አልተቻለም ብለዋል።ከዛም አልፎ የአማራ ተወላጆቹ ከታፈኑ በኋላ የሚወሰዱበት ቦታ አለመታወቁ ደግሞ ነገሩን አሳሳቢ አደርጎታል ብለዋል።


በአካባቢው በየጊዜው ንጹሃን የአማራ ተወላጆች ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻ የሚፈጽመውና ቤተመንግስቱን ከተቆጣጠረው አካል መመሪያ የሚሰጠው ይሄው ገዳይ ቡድን በአዲስ መልኩ በአካባቢው አፈናና ዝርፊያ መጀመሩን ይናገራሉ።


መሬትም ሆነ መኖሪያ አልባ የተደረገው የአማራ ህዝብ ደግሞ የሚዘረፈው አይደለም የሚላስ የሚቀመስ ካጣ አመታት አስቆጥሯል ሲሉ ምንጮቹ ሁኔታውን ገልጸዋል።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አስፍረዋል። ከዚህ በፊት ይሄው ተመሳሳይ ድርጊት የትግራይ ተወላጅ በሆኑ የአየር

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ ቡድን አሁን አንድ ቦታ በከተማው ፒያሳ ተብሎ በሚጠራውና ደሴ መውጫ ላይ ብቻ መሆኑን ነው የተናገሩት

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰ

Comments


bottom of page