በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ እንጦጦ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የመከላከያ ሃይልን ልብስ የለበሰው ሃይል በስርቆትና በማስፈራራት ወንጀል ላይ ተሰማርቷል ሲሉ ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ከስርቆቱም በላይ ለቱን በተኩስ ሲያምሰው የሚያድረው አካል ህብረተሰቡን ለመረበሽ የሚሞክረው አካል ማንነቱ የማይታወቅ ነው ይላሉ።
ራሱ የመከላከያ ሃይል ነኝ ብሎ ካምፕ ተሰቶት የተቀመጠው ስብስብ ራሱ ሌባ ነው ይላሉ።
እቤት ውስጥ በመግባት ጭምር ዝርፊያ የሚፈጽመው ይሄው አካል ህብረተሰቡን መሄጃ አሳጥተውታል ብለዋል።
በአካባቢው ቤቶች መፍረስ ከጀመሩ ጅምሮ አካባቢው ሰላም አግኝቶ አያውቅም ይላሉ።
ከዚህ ውስጥ ደግሞ አብረዋቸው የኖሩ የኦሮሞ ተወላጅ ወጣቶች እንደሚገኙበትም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ይሄው ህገወጥ ቡድን ሌብነቱንም ሆነ ማሸበሩን የሚፈጽመው ደግሞ ከቦታ ቦታ በመቀያየር ነው ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።