top of page

ግንቦት 17/2015 የባህር ዳር ከነማ እግር ኳስ ቡድን ደጋፊዎች ላይ የቦምብ ጥቃት ተፈጸመ!


የባህር ዳር ከነማ እግር ኳስ ቡድን ደጋፊዎች ላይ ዛሬ የደረሰውና ለ 23 ሰዎች መጎዳት ምክንያት የ ሆነው የቦምብ ጥቃት የፈጸመው ወደ ክልሉ አስቀድሞ እንዲገባ የተደረገው የኦህዴዱ አደገኛ የጥፋት ቡድን መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች አጋለጡ።


ይሄ ቡድን በተደራጀ መልኩ ክልሉን ለማጥፋት ወደ አካባቢው የገባው ሲሆን ክልሉን ለማጥፋት አጀንዳ ይዞ የገባው ነው ይላሉ።


ዛሬ በባህርዳር ከነማ የእግር ኳስ ቡድን ደጋፊዎች ወደ ሐዋሳ ለመጓዝ በመዘጋጅት ላይ ሳሉ የተፈጸመው የቦምብ ጥቃትም የዚሁ የጥፋት አጀንዳ ዋና አካል ነው ብለዋል።


ይሄ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ የከተማዋን ከንቲባ ጨምሮ ባልታወቀ ሃይል ጥቃቱ ተፈጸመ በዚህም ወደ 23 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል የሚል መግለጫ እንዲያወጣ ቢደረግም ያ ሁሉ ከእውነት የራቀ ነው ይላሉ።


ዋናው የዛሬው ጥቃት ጎንደርና ጎጃም ብሎ የመከፋፈል አጀንዳ ሲሆን ይሄ ደግሞ በማህበራዊ ድረገጽ ጭምር ተቆርቋሪ በሚመስሉ አካላት እንዲናፈስ ተደርጓል ይላሉ።


ነገር ግን የዛሬው ቦምብ ጥቃት ክልሉን የማጥፋቱ ዘመቻ ጅማሬ ነው የሚሉት ምንጮቹ ይሄ የጥፋት ሃይል አሁን በመጀመረው መንገድ አማራን በመከፋፈል ክልሉን የማውደም አጀንዳውን ይቀጥላል ብለዋል።


የጥፋት ሃይሉ ዛሬ በጀመረው መንገድ ባህርዳርን ጨምሮ በጎጃም የተለያዩ መስመሮች ከባድ ጥቃት ለመፈጸመ አካባበቢዋችችን ለይቶ ጨርሳል ሲሉም ተናግርዋል።


ለዚህ ደግሞ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኦህዴዱ ሃይል መሰመራቱንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


በተለይ ጎጃምና ጎንደር አንድ ላይ ከሆኑ ዋጋ የለንም የሚለው የአብይ አህመድ ቡድን ይሄንን የህብረተሰብ ክፍል መነጣጠልና ቂም እንዲያያዝ ለማድረግ የዛሬውን አይነት ጥቃት መፈጸም ዋናው የአጀንዳው ማስፈሚያ ተደርጎ ተቀምጧል ብለዋል።


የአማራ ብልጽግና በተለይ በቅሬታ ላይ ያለውን የታችኛውን አመራር በተቻለ አቅም ማሸማቀቅና ችግር ውስጥ ማስገባት ከዛም አልፎ ሁሌም አንገቱን ደፍቶ እንዲኖር ማድረግ የሚለው ደግሞ በመመሪያ ጭምር የወረደ ነው ይላሉ የውስጥ ምንጮቹ።


ለዚህ ደግሞ አስቀድሞ ጎጃምና አካባቢውን በዚሁ አደገኛ ቡድን እንዲወድም ማድረግ የኦህዴዱ ስብስብ አጀንዳ ነው ሲሉም የኢትዮ 360 ምንጮች እውነታውን አጋልጠዋል።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

Comments


bottom of page