top of page

ግንቦት 17/2015 የኢዜማ ፓርቲን በበላይ ሲመሩ የቆዩ አመራሮች ተለዮ።



የኢዜማ ፓርቲን በበላይ ሲመሩ የቆዩ አመራሮች ከፓርቲው መለየታቸውን አስታወቁ።


አመራሮቹ በተስፋ በቀረው የለውጥ ጅማሮ አንድ ትልቅ ሀገራዊ ፓርቲ እንደሚያስፈልግ አምነውና ያላቸውን አዋተው “ኢዜማ” የሚባል ሁሉን አሰባስቦ የሚያቅፍ፣ ለአንድነት ኃይሉ መሰባሰቢያ ይሆናል ብለው በማለው ሀገር አቀፍ ፓርቲ እንዲሆን መመሥረታችውን ያስታውሳሉ።


ኢዜማ ፓርቲ ውስጥ በአንዳንዶቻችን መካከል መጠነኛ የአቋም ልዩነት ቢኖርም በሂደት በወያየት እንዲሁም መሬት በረገጠ ሥራ ወቅት ልዩነቱ እየጠበበ እና እየተስተካከለ ይሄዳል በሚል ቅን እሳቤ፤ በወንድማማችነት መንፈስ አምነው መቀበላቸውን ለኢትዮ 360 በላኩት መግለጫ ላይ አስፍረዋል።


ሆኖም ብዙም ሳይቆይ የአቋም ልዩነቱ ላይ የአካሄድም ልዩነት ተጨምሮበት ትግላቸው መስመር ስቶ ከፍተኛ በሆነ በውስጠ ፓርቲ ትግል ውስጥ ተጠልፈው እንዲቆዩ መደረጋቸውን ያነሳሉ።


የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ገጥሞት የማያውቅ እዚህ መከራ ውስጥ ከመግባቱ በፊትም መንገዳችንን እንድናስተካክል በሚል በፓርቲው ውስጥም በብዙ መታገላቸውን ሳይጠቁሙ አላለፉም፡፡


ከዚህ ሁሉ ትግል በኋላ ግን ነገሩ መስተካከል ባለመቻሉ ከፓርቲው በይፋ መለየታቸውን በመግለጫቸው ይፋ አድርገዋል።


በይፋ ከፓርቲው መሰናበታቸውን ከገለጹት መካከልም አቶ የሽዋስ አሰፋ፣ ወ/ሮ ናንሲ ውድነህ፣ አቶ ሀብታሙ ኪታባ፣ አቶ የጁአልጋው ጀመረ፣ አቶ ተክሌ በቀለ፣አቶ ኑሪ ሙደሲርና አቶ ዳንኤል ሺበሺ እንደሚነኙበትም አስታውቀዋል።



ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦህዴድ/ብልጽግና ስርዓት ከአሳዳጊያቸው ከህወኃት ውድቀት መማር የማይችሉ ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች ስለሆኑ ህዝቡ አምርሮ ሊታገላቸው ይገባል ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ጥሪውን አቀረበ።


ህዝቡ በቤቱ ውስጥ ተቀምጦ ይህንን አምባገነን መንግሥት ከማማረር በዘለለ ተቃውሞውን ወደ አደበባይ በመውጣት ሰላማዊ ህዝባዊ ትግሉን ማቀጣጠል ያስፈልገዋል ብሏል ለኢትዮ 360 በላከው መግለጫው ላይ፡፡


የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎችም መንግሥት በየጊዜው ከሚሰጠው ትንንሽ አጀንዳዎች በመውጣት መንግሥታዊ ለውጥ ወደሚያመጣ ትግል ፊታችሁን እንድታዞሩ ሲል ባልደራስ ጥሪውን አቅርቧል።

 
 

Recent Posts

See All
መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

 
 
መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

 
 
መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

 
 

Email: ethio360dgre@gmail.com

Phone: 540-277-3242

Donate with PayPal

© 2023 by Ethio360 Media

Connect with Us

  • rumble
  • Telegram
  • TikTok

Support Us

Advertise With Us

bottom of page