በኦሮሚያ ክልል የሚገኙና በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጅ ምሁራን መንግስት ነኝ የሚለው አካል በሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚያደርገውን ህገወጥ እንቅስቃሴ በአስቸኳይ ማቆም አለበት ሲሉ አሳሰቡ።
በአቢይ አህመድ የሚመራው ብልፅግና ይላሉ ምሁራኑ ለኢትዮ 360 በላኩት መልዕክት ላይ የጹሃንን ቤት እያፈረሰ ይገኛል ብለዋል።
በቤቶች ያልበቃው ይሄው አካል መስጊዶችን ወደ ማፈራረሱ ተሸጋግሯል ሲሉ ያስቀምጣሉ።
መፈንቅለ መጅሊስ ያደረገውና መንግስት ነኝ የሚለው አካል የህዝበ ሙስሊሙ ድምፅ እንዳይሰማ ማድረግ ችሏልም ሲሉ ሁኔታውን አስቀምጠዋል።
አሁን ደግሞ ቅዱስ ሲኖዶስን የመቆጣጠርና የመዋጥ ተግባር ላይ በቀጥታ እየተሳተፉ ነው ይላሉ በመረጃቸው ላይ።
በቅርቡም እንደ መስጊዶች ሁሉ ቤተ ክርስቲያናትን ለማፍረስ አቅዷል ሲሉ ምሁራኑ ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ ገልጸዋል።
በኦሮሞ ህዝብ እየማለ ስልጣን የተቆጣጠረው ብልፅግናን እኛ የኦሮሞ ምሁራን ይህን ተግባሩንን እንዲያቆም እንጠይቃለን ሲሉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
የኦሮሞን ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ለመለያየት የብልፅግና መንግስት እየሄደበት ያለውን እርቀትንም አጥብቀን እንቃወማለን ብለዋል።
ሀይማኖታችንን ለእኛ ለአማኞቹ ተውልን ያሉት ምሁራኑ ይሄ የማይሆን ከሆነ ደግሞ ከቀጣዩ ጊዜ የከፋ ይሆናል ሲሉም ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።