በደብረብርሃን ጠባሴ ክፍለ ከተማ ተከራይተው ከሚኖሩበት ቤት በድንገት ውጡ የተባሉት የከተማዋ ነዋሪዎች መሄጃ አተው ችግር ላይ ወድቀዋል ሲሉ ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
በክፍለ ከተማው በንጉስ ሳህለ ስላሴ ቀበሌ ነዋሪው የሆኑት ተከራዮች አቀድሞ በአስር ቀን እንዲወጡ ከታዘዙ በኋላ እሱ ተቀይሮ ዛሬውኑ ልቀቁ መባላቸው መሄጂያ እንዲያጡ አድርጓቸዋል ይላሉ።
በድንገት ከቤታችሁ ውጡ የተባሉት እነዚህ ነዋሪዎች የኪራይ ቤት እንዳያገኙ እንኳን በተፈናቃይ በተሞላው የደብረብርሃን ከተማ ውስጥ የኪራይ ቤት ማግኘት ከባድ ሆኑላ ሲሉ ሁኔታውን ያስቀምጣሉ።
እነዚህ ነዋሪዎች ቤቱን በድንገት እንዲለቁ የተደረጉት ደግሞ ራሱ ነዋሪውን ለመግደል ወደ አካባቢው ለሚገባው የኦህዴዱ ሃይል ነው ይላሉ።
ነዋሪውን በዚህ መልኩ እያጣደፈ ሜዳ ላይ እንዲወድቁ ያደረገው የቤቱ ባላቤት ባለሃብት ቤቱን መሳሪያውን ጠምዶ ህዝብን ለመጨረስ እቅድ ላለው አካል ለማስረከብ ነው ሲሉም በሃዘኔታ ገልጸዋል።
የከተማዋ ነዋሪ የሆነውና ቀማው የተባለው ይሄው ባለሃብት ከማንም እውቅና ውጪ ይሄንን ሃይል ወደ እሱ ቤት ለማስገባት ዞን ላይ የጨረሰው ጉዳይ ሳይሆን አይቀርም ሲሉም ግምታቸውን ያስቀምጣሉ።