ግንቦት 22/2015በፌደራል መስሪያ ቤቶች የሚመጡ የትምህርት እድሎች ለአማራ ተወላጆች እንዳይሰጡ መመሪያ መውረዱን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።
- Ethio 360 Media 2
- May 30, 2023
- 1 min read
በፌደራል ፓሊስ ዉስጥ የበዛና ግራ የሚያጋባ ስራ እየተሰራ ነዉ የሚሉት ምንጮቹ አንዳንድ የዉጭ ሀገር የትምህርት እድል ሲመጣ በግልፅ አማራ እዳይከተት የሚል መመሪያ ከእያንዳንዱ አመራር መሰማቱን ቀጥሏል ይላሉ።
የትምህርት እድሉ በብዛት ለባለጊዜዎቹ የሚሰጥ ሲሆን ለደቡብ ተወላጆች የሚሰጥ እድል ካለ ደግሞ የጉራጌ ተወላጆችን እንዳያካትት የሚለውም በመመሪያ ደረጃ የወረደ ነው ብለዋልምንጮች።
የአማራ ተወላጆችም ሆኑ የጉራጌ ተወላጆች በውጭ ሃገር የትምሀር እድል እንዳይሳተፉ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ጥቅማ ጥቅም ያስገኛሉ በሚባሉ ጉዳዮች ውስጥም የአማራና ተጉራጌ ተወላጆች አይካተቱም ብለዋል።
ምናልባትም አሁን ላይ ያለው ሰው በላው ስርአት እየሄደበት ያለው ርቀት አንድና ሁለት ብሔርን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ኢትዮጵያ ወደ ህዝባዊ እምቢተኝነት እንዲሄድ የሚያደርግ ነው ሲሉ አዝማሚያውን ያስቀምጣሉ።
በተለይ ደግሞ በፌደራል ፖሊስ፣በመከላከያ፣በደህንነትና በአጠቃላይ በጸጥታው ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች ላይ የሚደረገው ጫና ነገሮችን ወደ ሌላ አቅጣጫ እየፉአቸውን ነው ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።