በደብረ ኤልያስ ገዳም የሚገኙ መነኮሳት፣ጸበልተኞችና ሕጻናት በኦህዴዱ የመከላከያ ሃይል በግፍ ታርደው መገደላቸውን መነኮሳቱ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ከትላንት ጀምሮ በከፍተኛ መሳሪያ ገዳሙንና ንጹሃንን እየገደለ ያለው አካል አሁንም ሃይሉን እያጋዘ ነው ይላሉ።
በገዳሙ በጥይት ተደብድበው ከሚገደሉት በላይ ህጻናት አይናቸው እያየ በግፍ ታርደው እንዲገደሉ ሆነዋል ብለዋል መነኮሳቱ።
አንድ ሙሉ በረት እንስሳትን የፈጀው አና ንጽሃንን በአሰቃቂ ሁኔታ የሚገለውን ቡድን በአካባቢው ያሉ የቤተክርስቲያኗ አባቶች ሊያወግዙት እንኳን አልፈለጉም ብለዋል።
አሁንም እየተናገሩ ያሉት ከ እዚ ገዳይ ቡደን አንተረፍለን በለው ሳይሆን አለም ይወቀው በሚል ብቻ ነው ይላሉ።
በስለትና በማደጎ የተሰጡና እድሜያቸው ከ11 አመት በታች የሆኑ የአብነት ተማሪ ህጻናት ታርደዋል፣የተረፉትም እጣ ፋንታቸው ምን እንደሆነ እስካሁን ማወክ አልተችለም ብለዋል።
ቤተክርስቲያኑ በእሳት እንዳይነድ ውሃ ይዘው ሲጠባበቁ የነበሩ እናቶችም በዚሁ ገዳይ ቡድን ተጨፍጭፈዋል ይላሉ መነኮሳቱ።
በህይወት የተረፉትም አይናቸው እያየ በዚሁ ስብስብ ታርደዋል ሲሉም በሃዘኔታ ይናገራሉ።
የገዳሙ ክፍል ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በንጹሃን አስከሬን ተሞልቷል የሚሉት መነኮሳቱ የእነሱም እንደሚገደሉ ቢያውቁም ገዳማቸውን ግን ጥለው ወዴትም እንደማይሄዱ ነው የተናገሩት።
ከባድ መሳሪያ በመጫን ጭምር አሁንም ይሃው ገድይ ቡድን ወደ አካባቢው እየተጋዘ ነው የሚሉት መነኮሳቱ የዚህ ገዳይ ቡድን ከባዱ ችግር በቋንቋ እንኳን የማይግባቡት መሆኑ ነው ብለዋል።
አሁንም ለወሬ ነጋሪ እንኳን ቢተርፍ በሚል በገዳሙ ያሉ መነኮሳትን፣ጸበልተኞችንና ህጻናትን ለማትረፍ እየጮሁ ቢሆንም እስካሁን ግን የደረሰላቸው አካል አለመኖሩን ነው መነኮሳቱ ለኢትዮ 360 የገለጹት።