top of page

ግንቦት 22/2015 የኦህዴዱ መከላከያ ሃይል መረሃቤቴና አካባቢውን ለማውደም አካባቢውን መውረሩን ተገለጸ! 360 ገለጹ።



ሰሜን ሸዋን በአራት አቅጣጫ የወረረው የኦህዴዱ መከላከያ ሃይል መረሃቤቴና አካባቢውን ለማውደም አካባቢውን መውረሩን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።



ከካራ ምሽግ ሚዳ መርሃቤቴን ጨምሮ ሶስቱ ወረዳዎቹ በአራት አቅጣጫ በዚሁ ሃይል ተከቧል ብለዋል።


ወደ መረሃቤቴ ሙሉ በሙሉ ለመግባት ከ60 ያላነሰ ኦራል ተሽከርካሪ ሙሉ ሃይል አስገብቷል ይላሉ።


ከአዲስ አበባ መስመር ይዞ ወደ ጀማ የገባውን ጨምሮ የደራ መስመርን ይዞ የገባው ሃይል በሙሉ አካባቢውን ለማውደም አካባቢውን እየወረረ መሆኑን ሳይጠቁ አላለፉም።


የወረይሉና ጃማን ይዞ ወደ መረሃ ቤቴ ያደረገው አካል ሰሜን ሸዋን የወረረው ሰሞኑን በካርታ ጭምር ያወጣውንና አካባቢውን ለመውረር የያዘውን እቅድ ለማሳካት ነው ብለዋል ነዋሪዎቹ።



እነሱ በዚህ ደረጃ ወረራ ሲያካሂዱ ማህበረሰቡ ደግሞ ፋኖን አናስነካም በሚል በጋራ ቆሟል ሲሉም ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።


የፋኖ ህዝባዊ ሃይልም ሆነ ህብረተሰቡ በዚህ ደረጃ ተከቦ ባለበት ሰአት ደግሞ አለም ከተማ ላይ ያለው የፖሊስ ሃይል ወደ ህብረተሰቡ መተኮስ ጀምሯል ይላሉ።



ይሄንን ደግሞ ስማቸውን ጭምር በማውጣት ለህዝቡ ማንነታቸውንም እንደሚያጋልጡ ነው ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 የገለጹት።


Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

bottom of page