top of page

ግንቦት 24/2015 በሰሜን ሸዋ እንሳሮ አካባቢ የገባው የኦህዴዱ የመከላከያ ሃይል በንጹሃን ዜጎች ላይ ተኩስ መክፈቱ ነተገለጹ።



በሰሜን ሸዋ እንሳሮ አካባቢ የገባው የኦህዴዱ የመከላከያ ሃይል በንጹሃን ዜጎች ላይ ተኩስ መክፈቱን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።



ከአዲስ አበባ 130 ኪሎ ሜትር ላይ የምትገኘውን የእንሳሮ ከተማ የወረረው የኦህዴዱ ሃይል አካባቢውን መውረር ብቻ ሳይሆን ንጹሃን ላይ ተኩስ ከፍቷል ብለዋል።



በዚህም አንድ የከተማዋ ነዋሪ ሲገደል ሌሎሎ ደግሞ መቁሰላቸውን ነው ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ ያሰፈሩት።



ከባባድ መሳሪያዎችን ጭምር በመያዝ ወደ አካባቢው የገባው ይሄ ሃይል ማህበረሰቡን ማሸበር ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ የለሚ ከተማን ዙሪያዋን ከቧታል ይላሉ።



በብዛት ሃይሉ ያስገባው ይሄው ገዳይ ቡድን መርሃቤቴ ላይ ሲደርስ አታልፍም በመባሉ ወደ እንሳሮ ማምራቱን ይናገራሉ።



ነገር ግን መርሃቤቴ ላይ መንገድ አታልፍም የተባለው ይሄው ሃይል አሁን ላይ መርሃ ቤቴ ላይ ቤት ለቤት መሳሪያ ለመንጠቅ እየሞከረ መሆኑንም ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ ላይ አመልክተዋል።



በዛው በሰሜን ሸዋ ከጃማ ወደ ሚዳ ሽማግሌዎችን በመላክ ነገሩን የማቀዛቀዝ ስራ ለመስራት እቅድ መያዙን የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።


አስቀድሞ ይላሉ በሽማግሌ ስም የጃማ አካባቢ ህዝባዊ ሃይልንም ሆነ ህብረተሰቡ ሲያነሳ የነበረው የህልውና ጥያቄ እንዲቀዛቀዝ ማድረጋቸውን ያስታወሳሉ።



አሁንም በተመሳሳይ መልኩ ሚዳ ላይ በሽምግልና ስም ህዝባዊ ሃይሉን መምታት፣አሉ የሚባሉና የህዝባዊ ሃይሉ መሪዎችን ማፈን ካልሆነም መግደል እቅድ ተደርጎ ተይዟል ይላሉ።



በተለያየ መንገድ የቀረውን የጥፋት አጀንዳ ሁሉ ለማስፈጸም የሚሰራው የኦህዴዱ ኦነግ ስብስብ የአማራ ክልልን ለማውደም የአማራ ተወላጆችንም ለመፍጀት ያለውን ነገር ሁሉ እየተጠቀመ ነው ሲሉም ያስቀምጣሉ።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

Comments


bottom of page