በአዲስ አበባ ሚኒዬም አዳራሽ ነገ የመከላከያ ዘጋቢ ፊልም ይመረቃል በሚል ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችና መመህራንን እንዲልኩ በግዴታ መታዘዛቸውን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
ከየትምህርት ቤቱ ሰላሳ ተማሪዎችንና አምስት መምህራንን እንዲልኩ በማስጠንቀቂያ ጭምር መመሪያ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።
ይሄ ብቻ ሳይሆን በየትምህርት ቤቱ መዝጋቢ ቡድን ተልኮ ተማሪዎችንና ምምህራንን መዝግቦ መሄዱን ገልጸዋል።
የተመዘገቡት ተማሪዎችም ሆኑ መምህራን የተለያዩ ምክንያቶችን በማስቀመጥ መገኘት እንደማይችሉ ለመግለጽ ቢሞክሩም መቅረት እንደማይችሉ ከማስጠንቀቂያ ጭምር እንደተነገራቸውም አመልክተዋል።
አብይ አህመድና አዳነች ምግብ እያቀረቡ አስምረው ማንም ልቅር የሚል ጥያቄ ማንሳት የለበትም በሚል ማስጠንቀቂያ እንደወረደላቸውም ነው የኢትዮ 360 ምንጮች የገለጹት።
Comentários