በአዲስ አበባ በተለምዶ ሽሮ ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የባህል አልባሳት መደብር ሙሉ በሙሉ መዘጋቱን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ለንግድ መደበሩ መታሸግ ዋናው ምክንያት ደግሞ አስቀድሞ መደብሮቹ ለታሪክ በማይቆረቆሩ ካድሬዎች እንዲሞላ በመደረጉ ነው ይላሉ።
የባለጊዜው የቀኝ እጅ መሆናቸው ደግሞ የአካባቢው ማህበረሰብ በተደጋጋሚ ይሄ እንዳይደርስና የሚፈጸመው ወንጀል ይቁም ሲል እነሱ ደግሞ ስርአቱን በመደገፍ ላይ ነበሩ ብለዋል ለኢትዮ360።
አሁንም ድምጽ ማሰማት የተጀመረው በራሳቸው ስለመጣ እንዲ በሌላ አይደለም ባይ ናቸው የሚል መሆኑን ያነሳሉ።
ነባሩን ኮንቴነሩን አፍርሶ ከአካባቢው ያባረረው አካል ቦታውን ያስረከበው ለካድሬዎች ስብስብ መሆኑን ያነሳሉ።
አሁንም እነዚህ የባህል አልባሳት መደብሮች እንዲፈርሱ እንዳይነሱ ተደርገው የተዘጉት እስር በርሳቻው ስላልተሳማሙ እንጂ ሌላ አይደለም ባይ ናቸው።
ሙሉ በሙሉ መደብሮቹን ያሸገው አካል አካባቢውን በገመድ ከልሎ በወታደር እያስጠበቀው ነው ብለዋል።
መደብሮቹን ተረክበው የነበሩት ሰዎች አሁን ላይ ጥቅማቸው ሲነካ ድምጽ ያሰሙ እንጂ ከእንጦጦ አምባ ትምህርት ቤት ችግር ጋር ተያይዞ ተማሪ ጠቋሚና አሳሳሪ በመሆን ሲሳተፉ እንደነበርም ያነሳሉ።
የአካባቢው ማህበረሰብ ይሄ ታሪካዊ ቅርስ እንዳይጠፋና አካባቢውም በዚህ ደረጃ እንዳይወድም ሲታገሉ መቆየታቸውንም ነው ለኢትዮ 360 የገለጹት።