የኦህዴዱ መከላከያ ሃይል በግሸን ማርያም ቤተክርስቲያን አካባቢ ሃይሉን ማስፈሩን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
ይሄ ሃይል በአካባቢው 020 ፣019 ፣021 ፣ 022 ፣023ና ሌሎች አካባቢዎች ላይ መፍሰሱን ጠቁመዋል።
በተለይ ሰሞኑን በአምባሰልና አካባቢው የፋኖ ህዝባዊ ሃይልን መሳሪያ አስፈታለሁ ብሎ በሞከረው የብአዴኑ ፖሊስና ሚሊሻ ስብሰብ ላይ የተወሰደው ርምጃ ለዚህ ሃይል ወደ አካባቢው መግባት ምክንያት ሆኗል ብለዋል።
በርካታ የጥፋት ሃይሉን በአካባቢው ያፈሰሰው የኦህዴዱ ሃይል በግሸን ማርያም አካባቢው መፍሰሱ ደግሞ ሌላ ጥያቄን አስነስቷል ሲሉም ምንጮቹ ተናግረዋል።
በደብረ ኤልያስ ገዳም የፋኖ ህዝባዊ ሃይል ተደብቋል የሚል የውሸት ትርክት በመያዝ መነኮሳትንና ጸበልተኞችን ከመጨረሱም በላይ ገዳሙ ላይም ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን ያስታውሳሉ።
አሁንም ይሄ የጥፋት ቡድን በዚህ አካባቢ መቶ መፍሰሱ ሌላ አጀንዳ ሊኖረው ስለሚችል ሁሉም አይኑን ወደዚሁ ቡድን እንዲያደርግ ሲሉም ምንጮቹ አሳስበዋል።
በተለይ ደግሞ በአራት አይሱዙ ተሽከርካሪ በአምባሰል ወረዳ 08ዲኖና 010 አካባቢ የሰፈረው ሃይል በቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ጥርጣሬን ከፍ አድርጎታል ብለዋል።
Comments