ግንቦት 29/2015
በፌደራል ፖሊስ እስካሁን በዜጎች ላይ ለፈጸሙት ኢ ሰብአዊ ድርጊት ማበረታቻ ዘመናዊ የተንቀሳቃሽ ስልክ ቀፎ ተገዝቶ ሊታደላቸው በዝግጅት ላይ መሆኑን ምንጮች አስታወቁ።
በፌደራል ፖሊስ መስሪያ ቤት ከመምሪያ በላይ ላሉ አመራሮች እስካሁን በዜጎች ላይ ለፈጸሙት ኢ ሰብአዊ ድርጊት ማበረታቻ ዘመናዊ የተንቀሳቃሽ ስልክ ቀፎ ተገዝቶ ሊታደላቸው በዝግጅት ላይ መሆኑን የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች አስታወቁ።
ይሄ አሰራር የተኮረጀው ደግሞ ዋናው የወንጀሉ መሪ ከሆነችው አዳነች ቢሮ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
በከንቲባዋ ቢሮ ቤት በማስፈረስ፣ንጹሃንን በማሳፈንና በማስገደል፣ነዋሪውን ሰላም በመንሳት ግንባር ቀደም ተሳታፊ ለሆኑ አመራሮ በዚህ መልኩ ማበረታቻ መቅረቡን ያስታውሳሉ።
እነዚህ ከመምሪያ በላይ ያሉ ሃላፊዎች የእነ አብይ ተዕልኮ አስፈፃሚ ባለጊዜው የኦህዴዱና የሆዳም አማራ ስብስቦች መሆናቸውን ያስቀምጣሉ።
ምስኪኑና ከታች ያለው ሰራዊት ግን የከተማዉን ነዋሪ ቤቱን እንዲያፈርስ ተደርጎ ሲያበቃ አሁን ደግሞ በካምኘ ተቸግሮ ላስቲክ ዘርግቶ የሚኖረዉን አባል በአስቸኳይ መጠለያውን አፍርሶ ሜዳ ላይ እንዲጥለው ትእዛዝ እንደወረደለትም ገልጸዋል።
ስርዓቱ ለሚያገለግለዉ ምስኪን ሰራዊት እንኳን እሚራራ ልብ የለዉም ሲሉ ጭካኔውን ይገልጻሉ።
እንደማሳያም የድሮዉ የኤርትራ ኤንባሲ ግቢ የነበሩ አባላቶቹን በአስቸኳይ ካረፉበት ቤት እንዲወጡና ሜዳ ላይ ከነሕጻናት ልጆቻቸው እንዲበተኑ መደረጉን አስቀምጠዋል።
በሰራዊቱ ላይ ይሄንን ጭካኔ እየፈጸመ ያለው አካል ለባለጊዜዎቹ ደግሞ ደሃ ቆጥቦ ካሰራው የጋራ መኖሪያ ቤት እየተመረጠ እንደሚሰጠው ያነሳሉ።
Comments