top of page

ግንቦት 9/2015 በሰሜን ሸዋ በይፋትና በሸዋ ሮቢት አካባቢዎች የኦህዴዱ የመከላከያ ሃይል በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት መክፈቱን ነዋሪዎቹ ለኢትዮ 360ገለጹ


በይፋት ባሱድ አካባቢ ማለዳው ላይ ጦርነት የከፈተው ይሄው ሃይል በከባድ መሳሪያ ቤቶችን ሲያወድም መዋሉን ይናገራሉ።


በዚህ ጥቃት አንድ ሰው የገደለው ይሄው ሃይል ሰሞኑን ለዚህ ዘመቻ ራሱን ሲያዘጋጅ መክረሙንም ጨምረው ገልጸዋል።


በባሱድ የጀመረውን ጥቃት ወደ ሸዋ ሮቢት ራሳና አካባቢው ያዞረው ሃይል በአካባቢው በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት መክፈቱንም ተናግረዋል።


በሸዋ ሮቢት ራሳ፣ማኔ አምባና ማፉድ ላይ ዛሬ በከባድ መሳሪያ ጦርነት የከፈተው ይሄው ሃይል ለሊቱን ሙሉ አዲስ ሃይል ወደ አካባቢው ሲያግዝ ማደሩንም ይናገራሉ።


የፋኖ ህዝባዊ ሃይልንም ሆነ ልዩ ሃይሉን ብሎም ማህበረሰቡን ትጥቅ ለማስፈታት አዲስ ዘመቻ ለመክፈት መዘጋጅቱን ኢትዮ 360 በመረጃው ማውጣቱ ይታወሳል።


ዛሬ በከባድ መሳሪያ በመታገዝ ጭምር የተጀመረው ጥቃት የዚሁ አንድ አካል ነው ብለዋል።


አዲሱ ዘመቻ ትጥቅ በማስፈታት የሚጠናቀቅ ሳይሆን አሉ የሚባሉ የህዝባዊ ሃይሉ አመራሮችን፣አባላትንና ለህዝባዊ ሃይሉ ድጋፍ ያደርጋሉ የሚባሉትን ሁሉ በጅምላ መጨርስ መሆኑንም የኢትዮ 360 ምንጮች ጠቁመዋል።


ሃይሉን በአዋሽ ፣ በሸዋ ሮቢት እና በማጀቴ በኩል ሲያግዝ የከረመው የኦህዴዱ ስብስብን ለማገዝ ህወሃት በተለያዩ አቅጣጫዎች ያስጠጋውን ሃይሉን ለጦርነት እያዘጋጀው መሆኑን ይናገራሉ።


በአፋር በኩል የሚያልፈውን ሃይል ህብረተሰቡ በተቻለ አቅም ለማገድ ቢሞክርም በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ድጋፍ ሰጪነት ይሄ ሃይል ወደ አካባቢው እንዲገባ እየተደረገ ነው ሲሉም ምንጮቹ ተናግረዋል።


በወሎና በጎጃም ብሎም በጎንደር ሃይሉን በተለያዩ አቅጣጫዎች አሰማርቶ የሚገኘው የኦህዴዱ ገዳይ ቡድን ወደ ቤንሻንጉልም ተሻግሮ ጦርነት መክፈቱንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


ይህ በእንዲህ እንዳለ በንጹሃን የአማራ ተወላጆች ላይ ጦርነት የከፈተው የኦህዴዱ ኦነግ ቡድን በቆላ ድባ ደግፉኝ የሚል ሰልፍ በብአዴን ካድሬዎች አስተባባሪነት ጠርቶ እንደነበር ምንጮቹ ይናገራሉ።


ነገር ግን በቆላ ድባ ጯሂት አካባቢ የተጠራውን ይሄንን ሰልፍ የአካባቢው ወጣትና የፋኖ ህዝባዊ ሃይል ፋኖ በጋራ በመሆን አክሽፈውታል ብለዋል።


የአካባቢው ማህበረሰብም ከልጆቻችን ጎን ነን በማለት የካድሬና የሚሊሻ ስብስብ ዞር በል ብሎ አባሮታል ሲሉ የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።


Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

bottom of page