በሰሜን ሸዋ ሃገረ ማርያምና አሳግርት በህዝባዊ ሃይሉ ቁጥጥር ስር ሲውሉ የሰው በላው ስርአት ደግሞ ሃይሉን ከደብረማርቆስ ወደሌሎች አካባቢዎች እያጋዘ መሆኑን የህዝባዊ ሃይሉ አባላት ለኢትዮ 360 ገለጹ።
ሀገረ ማርያምና አሳግርትን ጨምሮ አካባቢውን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይሉ የቡልጋ ቀጠናን ሰላም አስከብሯል ብለዋል።
ከማርቆስ ግዳጅ በሚል የግለሰቦችን ተሽከርካሪ እየቀማ ያለው የሰው በላው ስብስብ ሃይሉን ከቦታ ቦታ እያዘዋወረ መሆኑን ነው አባላቱ የሚናገሩት።
ወደ አማኑኤልና ወደ ፈረስ ቤት ሃይሉን እያዘዋወረ መሆኑን የሚናገሩት የህዝባዊ ሃይሉ አባላት መከላከያ በሚል ወደ አካባቢው እየገባ ያለው ቡድን እንኳን ሃገር ክልልም የሚጠብቅ አይደለም ብለዋል።
በገፍ እየገባ ያለው ሃይልም በገባበት እንደማይወጣ በእርግጠኝነት እንናገራለን ብለዋል ለኢትዮ 360.
የገዳዩ ቡድን ስብስብ ልብሱን ቀያይሮም ሆነ በምንም መልኩ ቢመጣ የአማራ ህዝብን ትግል ማሸነፍ አይችሉም ብለዋል።
ራሱ አማራውን ሊገል የመጣው ሃይል ከአንገት በላይ እንጂ በታች የማይመታውን የህዝባዊ ሃይሉን በማድነቅ ስራ ተጠምዷል ሲሉ አማኑኤል ላይ የሆነውን ይናገራሉ
ይህ በእንዲህ እንዳለም ዛሬ መርዓዊና ቢኮሎ ላይ ገዳዩ ቡድን የከፈተውን ተኩስ ተከትሎ ከባድ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን ነው የኢትዮ 360 ምንጮች የሚናገሩት።
የመርዓዊና የቢኮሎ አጎራባች የሆኑት የይስማላ፣ የዱርቤቴ፣ የደቡብና የሰሜን አቸፈር ህዝባዊ ሃይሉ አባላትና ማህበረሰቡ ከጎናቸውን እንዲሆንም ጥሪያቸውን በማቅረብ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በሰሜን ሸዋ ጅሁር እንዋሪ አካባቢም ይሄው ገዳይ ቡድን በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት መክፈቱን ምንጮቹ አመልክተዋል።
በተጨማሪም በኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መኮይ አፍላ ላይ ገዳይ ቡድኑ ወደ ንጹሃን ዜጎች ላይ በተመኮስ ጭምር ከባድ መሳሪያ እያስወነጨፈ መሆኑን ነው የገለጹት።
ይሄው የገዳዮች ስብስብ በላስታ እና በቡግና ንጹሃንን በግፍ እየገደለና አይን ያወጣ ዝርፊያ እያካሄደ መሆኑን የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።
በትናንትናው አመሻሽ ከብልባላ ወደ ላልይበላ እየተጓዘ የነበረና ከ2.5 ሚሊየን ብርን ይዞ ይጓዝ የነበረን የጸደይ ባንክ ተሽከርካሪን መዝረፋቸውን ይናገሉ።
ንብረትን መጠበቅ እንጂ መዝረፍን ልማዱ ያላደረገውን የአማራ ህዝባዊ ሃይልን ዘረፈ ለማለት ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል ብለዋል።
የምስራቅ አማራ ፋኖው ሻለቃ አርበኛ ምሬ ወዳጆ ደግሞ ሌላ አጀንዳ የለንም”.. “ከሙስሊሙም ከክርስቲያኑም የተወልድን ነን፣ወሎን አደራጅተን ሸዋ ዘልቀን ተቀናጅተን፥ 1 የጋራ ጠላታችን እየታገልን መሆኑ ይታወቅልን ሲል በግልጽ አስቀምጧል።
ሻለቃ አርበኛ ምሬ ወዳጆ የአማራ ህዝባችን ዳግም እንዳይዋረድ ነው ግንባር ፈጥረን የምንታገለው። ሌላ አጀንዳ የለንም ሲልም ባስተላለፈው መልእክቱ ላይ አስምሮበታል።