top of page

ጳጉሜ 2/2015የቱሪዝም ሚኒስቴር የወር የቢሮ ኪራይ ሒሳብ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር መሆኑን ምንጮች አስታወቁ።



የቱሪዝም ሚኒስቴር የወር የቢሮ ኪራይ ሒሳብ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ሲሆን በየቀኑ ለምግብ ብቻ ከ300ሺ ብር በላይ ወጪ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች አስታወቁ።


በሚኒስትሯ ናሲሴ ጫሊ ትእዛዝ ለቢሮ እቃና ለኢንተርኔት አገልግሎት በሚል ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉን ተናግረዋል።


በወር 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ኪራይ ወደ ሚከፈልበት ቢሮ እንዲገባ የተደረገው ሰራተኛን መብት ከግምት ያላስገባው የናሲሴ ጫሊ አስተዳደር በየቀኑ እዛው ቦሌ አካባቢ ካለ ታዋቂ ሆቴል ምግብ በገፍ እያስጫነ ለሚያስመጣውና ብፌ በማድረግ ሲበላ ለሚውለው ምግብም ከ3መቶ ሺ ብር በላይ ወጪ እንደሚሆን አስምረውበታል።


በሁሉም መልኩ እየተበደለ ያለው ሰራተኛ ግን ከዚህ ቢፌ ተቋዳሽ አይደለም ሲሉ በየቀኑ ከሆቴሉ የሚላከውን የሒሳብ ደረሰኝ ዋቢ በማድረግ አጋልጠዋል።


በናሲሴ ጫሊ የሚመራው ቡድን በዚህ መልኩ ሲንደላቀቅ ሌላው ሰራተኛ ግን የሰራበትን ደሞዝ በሰአቱ ማግኘት እንደሰማይ ርቆታል ይላሉ።


አሁን ላይ ሰራተኛው ደሞዙን ለማግነት በትንሹ አንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን መጠበቅ ግዴታው ነው ሲሉ ያለውን ህገወጥነት አጋልጠዋል።


የዚህን ወር ደሞዝ ሰራተኛው እስካሁን ያላገኘ ሲሆን እነ ናሲሴ ግን በሰራተኛው ደሞዝ ራሳቸውን ማሽሞንሞናቸውን ቀጥለዋል ሲሉ የውስጥ ምንጮቹ ተናግረዋል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ ቱሪዝም ሚኒስቴር ፤ ቅርስ ጥበቃ ፤ ዱር እንሰሳ በጋራ በቅርስ ጥበቃ አዳራሽ ሰራተኛውን ሰብስበው እንደነበር ያነሳሉ የኢትዮ 360 ምንጮች።



በዚህ ስብሰባ ላይ ስለሃገራዊ ጉዳይ እንደሚወያይ የተነገረው ሰራተኛ የእጅ ስልክን ጨምሮ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያን ይዞ መግባት እንደማይችል ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠውም ሳይጠቁሙ አላለፉም።


በዚህ ስብሰባ ላይ አስገራሚው ንግግር የነበረው የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተር ነኝ ከሚለውና ረ/ፕሮፌሰር የሚል ማዕረግ ከያዘው አበባው ከሚባለው ግለሰብ የወጣው ንግግር ነው ይላሉ።


ይሄ ግለሰብ ለተሰበሰበው ሰራተኛ ደብረኤሊያስ የሚባል ገዳም የለም፣ በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥም አይታወቅም፣ ገዳም የተባለውም ገዳም ሳይሆን ማሰልጠኛ ነው በሚል በድፍረት መናገሩን ምንጮቹ አስታውቀዋል።


እሱ ማሰልጠኛ ብሎ በጠራው ገዳም ውስጥ በርካታ የእንጀራ ምጣድ መኖሩንና ከጀርባው ደግሞ ከጀርባው ማሰልጠኛ አለ፣ የአማራ ክልል ጦርነትም የተጀመረው ከዛ ነው በሚል በድፍረት ማብራሪያውን ሲሰጥ ተሰብሳቢው ሁሉ በአግራሞት ይመለከተው ነበር ብለዋል።


አሁን ላይ በአማራ ክልል እየተዋጋ ያለውም ዘራፊና አውዳሚ ቡድን ነው የሚሉና የአማራውን ማህበረሰብ የሚያጥላላ ስድብ በስብሰባው ላይ በድፍረት ሲናገር የዱር እንስሳ ጥበቃ ዳይሬክተሩ ኩመራ ያለምንም አስተያየት ስብሰባውን ጥሎ መውጣቱን ይናገራሉ።


የቱሪዝም ሚኒስትሯ ናርሲሴ ሰራተኛውን በመደለል እንዲያወሩ ለማግባባት ብትሞክርም መድረኩን በንቀት ሲመለከት ከነበረው ተሰብሳቢ ግን ምንም መልስ ሳያገኙ ስብሰባው ተበትኗል ብለዋል።


ሆድ አደርና ስርአቱን በገሌነት የሚያገለግሉ አንዳንድ ሰራተኞች ሃሳብ ለመስጠት ቢንፈራገጡም የብዙሃኑን ዝምታ ግን መስበር ሳይችሉ ቀርተዋል ብለዋል የኢትዮ 360 ምንጮች።

Recent Posts

See All

መስከረም 17/2016 በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰራተኞች እየታደኑና እየታፈኑ መሆኑን ሰራተኞቹ ገለጹ። ሰራተኞቹ እየታፈኑ ያሉት ደግሞ በውስጥ በተሰገሰጉ የሰው በላው ስርአት ሃይሎች ጥቆማ ሰጭነት መሆኑን ለኢትዮ 360...

መስከረም 17/2016 በሰሜን ሸዋ ሚዳ መርሃቤቴ ላይ ገድይ ያደረገ ህዝባዊ ሃይሉ በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎችን ከሰው በላይ ሃይል ነጻማውጣታቸውን ገለጹ

መርጦ ለማርያምን ነጻ ያወጣው ህዝባዊ ሃይል መቅደላ አምባ አምባ ዩኒቨርስቲ ውስጥና በአካባቢው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ መሽጎ የነበረውን ይሄንን ሃይል ማጽዳት ተችሏል ብለዋል። አሁን ላይ ከሁሉም አካባቢ የተባረረው ገዳይ...

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ

መስከረም 17/2016 አርሶ አደሮችን በግፍ የረሸነውን ገዳይ ቡድን በአካባቢው ያለው የመብረቅ ብርጌድ ጓሌ ሻለቃ ተከታትሎ በወሰደው ርምጃ ሁሉንም ማጽዳቱን ገለጹ። በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ የጭንጫዬ አርሶ...

Comments


bottom of page