በአዲስ አበባ ዙሪያ በተለያዩ ማጎሪያ ስፍራዎች ከሚገኙ ንጹሃን ዜጎች 150 ያህሉ በወረርሽኝ ህይወታቸው ማለፉን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
በተለይ የነዚህ ንጹሃን ዜጎች ህይወት ያለፈው በገላን፡በቡራዩ፣በሰበታ በሚገኙ ማጎሪያ ስፍራዎች ከሚገኙት ታራሚዎች መካከል መሆኑንም ነው ምንጮቹ ያመለከቱት።
ህይወታቸው ካለፈው አብዛኞቹ ደግሞ የአማራ ተወላጆች መሆናቸውንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
እነዚህ በግፍ ህይወታቸው ያለፈው ንጹሃን ዜጎች አስከሬንም በኦህዴዱ የመከላከያ ተሽከርካሪ ሌሊቱን ሲያጓጉዙ ማደሩን ተናግረዋል።
በስተመጨረሻም አነጋጉ ላይ በብላቴ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጀርባ በሚገኘው ጫቃ አስከሬናቸው እንዲቀበር መደረጉንም አጋልጠዋል።
ኦቪድ ኮንስትራክሽንን የሚመሩት የገዳዩ ቡድን ተባባሪዎች አሁንም በየቦታው የማጎሪያ ስፍራዎችን በመገንባት ንጹሃንን እያስጨረሱ ነው ሲሉም ምንጮቹ አስታውቀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በመራዊ ከተማ መንገድ ላይ እና ካፌ ውስጥ ተገኝተው የታፈኑ 17 ወጣቶችን በተለምዶ ቻይና ካምፕ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከወሰዷቸው በኋላ ገደል በማስቆፈር እዛው ገደል ላይ እንዲረሸኑ መደረጉን የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።
ይሄንን አይነቱ አስነዋሪ ድርጊት እየተፈጸመ ያለው ደግሞ የገዳዩ ቡድንና አድማ ብተና በሚል በአካባቢው የተሰማራው ሃይል መሆኑን ሳይጠቁሙ አላለፉም።
ከዚህም ሌላ በጎጃም አዊ ዞን አዲስ ቅዳም ከተማ አንድ አባት በዚሁ የአድማ ብተና ልብስ ለብሶ ወደ አካባቢው በገባ ቡድን በስለት መዋጋታቸውንም ተናገረዋል።
በወቅቱ ይላሉ ምንጮቹ በ3 ፓትሮል ዲሽቃ የታጠቁ የአድማ ብተና ልብስ የለበሱ ሃይሎች እያለፉ በነበሩበት ሰአት በቁጭት የልጃቸውን ስም በመጥራት ሲያዝኑ የነበሩ አባትን መመልከቱን ገልጸዋል።
ይሄው ስብስብ ከፓትሮል ወርዶ በቀጥታ ወድ አዛውንቱ ከመጣ በኋል በስለት ወግቷቸው መሄዱን ምንጮቹ ተናግረዋል።
ይሄ ስብስብ ይሄንን አሳዛኝ ድርጊት የፈጸመው ደግሞ ህዝብ በተሰበሰበበት መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።
በጩቤ የተወጉት አዛውንት የፋኖ አስር አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ አባት መሆናቸውንም ምንጮቹ ተናግረዋል።
ፋኖ አስር አለቃ ኤፍሬም የፋኖ መስራችና በተለያዩ ቦታወች በሽዎች የሚቆጠሩ ፋኖዎችን ያሰለጠነ ፣በህዋት ጦርነት የጋሸናን ምሽግ ሰብሮ የተሰዋ ጀግና ልጃቸውን ስም ስለጠሩ ብቻ በስለት ተወግተዋል ሲሉ ምንጮቹ በሃዘን ተናግረዋል።
አባትዬው በጩቤ ከተወጉ በኋላ አሁን ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ እንዳልተቻለም ምንጮቹ አመልክተዋል።