ከትግራይ እዳጋ ሰሉሰ የተነሳው 11ኛ ክፍለ ጦር በጠለም ወደ ሚገኘው ደቂ ገብራይ ቀበሌ መሻገሩን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
ከእዳጋ ሰሉስ የተነሳው ይሄው ጦር ወደ ደቂ ገብራይ ከመጣ በሁዋላ አስቀድሞ ወደ አካባቢው እንዲገቡ ከተደረጉት 3 ክፈለ ጦሮች ጋር እንዲቀላቀል መደረጉን ነው ምንጮቹ የገለጹት።
ህወሃት ጦሩን በዚህ መልኩ ኣያዘዋወር ባለበት ሰአት ቤተመንግስቱን የተቆጣጠረው ሰው በላው ስብስብ ደግሞ ህዝበ ውሳኔ በአስቸኳይ መካሄድ አለበት እያለ ህዝቡን በማስገደድ ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
በአካባቢው ነባር የሚባሉ አስተዳዳሪዎችንም ከሃላፊነታቸው በማስነሳት ወደ ተለያዩ ቦታዎች በመላክ አካባቢውን በሰራዊቱ ስር እንዲተዳደር እያደረገ ነው ሲሉም አጋልጠዋል።
ህወሃት አሁንም በአካባቢው ከባድ ተጽእኖ እያደረሰ ነው ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ፌደራል ላይ ከተቀመጠው አካል የተገባለት ቃል የልብ ልብ ስለሰጠው ነው ሲሉ በአካባቢው እየተፈጸመ ያለውን ድርጊት አመልክተዋል።
ነገር ግን ይሄ ሁሉ ድርጊት እየተፈጸመ ባለበት ሁኔታ ውስጥ ማንም ሊመለከተው ካልቻለው ሕዝብ በዚህ አመት ብቻ እስካሁን ከ200 በላይ ሰዎች በርሃብ እንደሞቱ የኢትዮ 360 የአካባቢው ምንጮች አጋልጠዋል::
ለትግራይ ክልል የመልሶ ማቋቋም ሰራ በጀት በጅቶ እያሰራሁ ነው የሚለው አካል ለጠለምትና አካባቢው የሚሆን ግን ምንም አይነት በጀት አለማቅረቡን ይናገራሉ።
የጤናና ሌሎች አገልግለቶችን በተመለከተም ሌሎቹ አካባቢዎች ተጠቃሚ ሲሆኑ የጠለምት ህዝብ ግን ለዚህ አልታደለም ሲሉ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ አጋልጠዋል።